እቴጌ ጣይቱና ዳግማዊ ምኒልክ

የአድዋ መሪዎች እቴጌ ጣይቱና ዳግማዊ ምኒልክ

አድዋ የኛ ብቻ ሳይኾን የአፍሪካውንና የመላው ጥቁር ሕዝቦች ድል ነው!

ጀግኞች አባቶቻችን ባደረጉት ተጋድሎ ኢትዮጵያ በነፃነት ኮርታ ኖራለች። አፍሪካውያን ወንድሞቻችንና በቅኝ አገዛዝ ቀንበር የነበሩ የዓለም አገራት የነፃነት ተስፋ የሰነቁትና የቅኝ አገዛዝን ፍጻሜ ትግል የጀመሩት በአባቶቻችን አብሪ ድል ብርሃን አግኝተው ነው።

የአውሮፓን ኃያል አገር ድል የነሱት ኃያልና ሀብታም ኾነው አይደለም። የተነሱበት ዓላማ እውነትነት፣ የነበሩ ልዩነቶቻቸውን አቻችለው እንደአገር በአንድነት በመቆማቸው፣ ጦርነቱንም ኾነ ዲፕሎማሲውን በጥበብ በመያዝ ጠላታቸውን ልቀው በመገኘት ድል አድርገውታል።

የአድዋ ዘመቻ የክተት አዋጅ
የአድዋ ዘመቻ የክተት አዋጅ

ዛሬ በእኛ ዘመን ከድህነት መውጣትና አባቶቻችን ያስረከቡንን ነፃነት አስጠብቀን የመኖር ግዴታ አለብን። ኢትዮጵያ ከአድዋ ወዲህ ብዙ ፈተናዎችን አሳልፋለች። ዛሬም ከባድ ፈተና ገጥሟታል። ነገም እንዲሁ። ያለፈውን አባቶቻችን በአቅማቸው የሚችሉትን አድርገው ተወጥተውታል። ነገ የመጪው ትውልድ እዳ ነው። ዛሬ ግን የእኛ ነው።

የአድዋ ተጋድሎ በቀጥተኛ ወረራ የተከሰተ ሲሆን፤ የዛሬው ደግሞ በድህነት፣ በክፍፍል፣ በትርምስ እንድንቆይ ከሚፈልጉ ኃይሎች ነው። የአድዋ ድል በተከናወነ በ124ኛ ዓመት ላይ፤ ኢትዮጵያ በራሷ ወንዝ በዓባይ ላይ ያላትን ተጠቃሚነት ለማሳጣት ድህነታችንንና መከፋፈላችንን የተመለከቱ ወገኖች ሊጨፈልቁን፣ ከአባቶቻችን ያነስን ሊያደርጉን ተነስተዋል።

አንተነህ እምሩ

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!