"… ስለውጭ ዜጎች ቀጠለች እቴጌ ”እኛ በጣም ቆንጆዎች ነን፣ ሰውነታችን ከለሩም ቅርፁም ያምራል። በዚህ ላይ በጣም ስለምናስደስታቸውና ንፁኅዎች ስለሆንን ይመስለኛል ዶላራቸውን መዥረጥ እያደረጉ የሚገዙት” እቴጌ ጨዋታዋን ትቀጥላለች። ዝሙት ለሷ የሻጭና የገዥ ጉዳይ ነው፤ የውሀ፣ የመብራት፣ የስልክ፣ የሠራተኛ ግብር … የማይከፈልበት እግዚአብሔር የሰጣት ምርጥ ቢዝነስ ነው። …"

 

ከላይ የሰፈረው ጽሑፍ የተወሰደው "ሦስት ሌሊቶችን ከጎዳና ዝሙት አዳሪዎች ጋር" በሚል ርዕስ በእንቢልታ ጋዜጣ ከወጣ ጽሑፍ ላይ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ ሦስት ሌሊቶችን ከጎዳና ዝሙት አዳሪዎች ጋር ያሳለፈችው በሀገር ውስጥ የሚታተመው የእንቢልታ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጽዮን ግርማ ነች ጽሑፉን ያስነበበችው። በዚህ መጣጥፍ ላይ ያየችውንና የሰማችውን እውነት ለንባብ አብቅታለች። የጎዳና ዝሙት አዳሪዎች ሕይወት ምን እንደሚመስል ለአንባብያን ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ሙሉ ጽሑፉን አቅርበነዋል። መልካም ንባብ! (ጽሑፉን በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ)

 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ