አስታውሳለሁ መቼ እረሳለሁ! የመጋቢት 1960 እልቂት በደቡብ አፍሪካ ሻርፕቪል ከተማ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፣ ነጻነት ለሀገሬ)

March 21, 1960 Sharpeville Massacre in South Africa

በየዓመቱ በአፍሪካ ውስጥ የተፈጸሙ ሁለት የህዝብ እልቂቶችን አስታውሳለሁ።

በወርሃ መጋቢት በደቡብ

አፍሪካ የጥቂት ነጮች የበላይነት ዘረኛ አገዛዝ/apartheid በሻርፕቪሌ ከተማ እ.ኤ.አ መጋቢት 21/1960 የፈጸመውን ዘግናኝ እልቂት አስታውሳለሁ። እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በህይወት በሌለው በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ልዩ ትዕዛዝ እ.ኤ.አ ሰኔ 8/2005 እና ከህዳር 1-10/2005 እንዲሁም ከ14-16 በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሓት) የጥቂት ጥቁሮች የበላይነት የጎሳ አገዛዝ/apartheid የተፈጸመውን አሰቃቂ እልቂት አስታውሳለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ነገሮች አዲስ የሚሆኑት፣ በእኛ ትናንትን መርሳት

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ይገረም አለሙ

People has been taken by federal police in south Ethiopia, Sumra.  በደቡብ ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሱምራ ብሔረሰብ አባላትን በገመድ አስሮ እየደበደበ አሰቃየ

ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ በሚኖሩ ዜጎች ላይ የተፈጸመን የባሪያ ፍንገላን ዘመን የሚያስታውስ ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚያሳይ ፎቶ በማኅበራዊ ድረ-ገጽ ተሰራጭቶ አጀኢብ ጉድ ብለናል። ነገሩ ትናንትን እየረሳን ዛሬ ለሚያጋጥመን ነገር አዲስ እየሆንን ጉድ ጉድ ለምንለው ለእኛ ነው እንጂ አዲስነቱ ለወያኔ ከበረሃ ጀምሮ አብሮት የኖረ ተግባሩ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፍርሃትም ይሸነፋል

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ተስፋዬ ገብረአብ

Prof. Ephraim Isaac ፕሮፌሠር ኤፍሬም ይስኃቅ

ዝነኛው አሸማጋይ ፕሮፌሠር ኤፍሬም ይስኃቅ መሰንበቻቸውን ሥራ እንደበዛባቸው ተሰምቷል። የኦሮሞን ህዝብ አመጽና ጥያቄ በሰላም ለመጨረስ እዚህም እዚያም እየደዋወሉ ልብ የሚነኩ እግዚአብሔራዊ ቃላት ተናግረዋል። የፕሮፌሠሩ ጥረት በደፈናው የሚነቀፍ ባይሆንም አይሳካላቸውም። የሽማግሌው የእርቅ መንገድ ጥሎ ማለፍ ይዘት እንዳለው ካለፈ ድርጊታቸው ትምህርት ተገኝቷል። በተጨማሪ ድርድር ወይም እርቅ ሲታሰብ መላ የኢትዮጵያን ህዝብ የመብት ጥያቄዎች ታሳቢ በማድረግ እንጂ፤ ጉልበት ካገኘው ኃይል ጋር ብቻ የመደራደር ዝንባሌ ያለፈውን ስህተት መድገም ይሆናል። በመሰረቱ ወያኔ በስውር ሽማግሌ መላክ መጀመሩ ጊዜ ለመግዛት ካልሆነ ከልብ እርቅና መደራደር ፈልጎ እንደማይሆን ይገመታል። ከፋፍሎ የማዳከም የህወሓት አካሄድ ገና ድሮ ተባኖበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ፤ አንድም በብልሀት - አንድም በጉልበት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይገረም አለሙ

TPLF / ህወሓት

ወያኔዎች ለትግል በረሃ ገባን የሚሉበት ግዜ የንጉሡ ሥርዓት ፈርሶ ኢትዮጵያ ወዴት እንደምትሄድ አይደለም የት ላይ እንደቆመች እንኳን በቅጡ ያልየበት ወቅት ስለነበር፤ ለብሶት ዳርጎ ወደ ጫካ የሚያስኬድ ቀርቶ ከተማ ተቀምጦ ለማኩረፍ የሚያበቃ በደል ነበር ለማለት አይቻልም። ስለሆነም ወያኔዎች በዛን ወቅት ለትግል የተነሱት የአጼ ዮሐንስን ቤተ መንግሥት ይዘው የትግራይን መንግሥት የመመስረት ህልማቸውን ለማሳካት መንግሥት አልባው ወቅት ምቹ ሆኖ ስለታያቸው ነበር። ቢዘገይም ካሰቡት በላይ ተሳክቶላቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዘ-ህወሓት በኢትየጵያ የታክሲ ሾፌሮች ላይ የከፈተው ጦርነት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፡- ነጻነት ለሀገሬ)

Ethiopian taxi drivers strike

በአሜሪካ “ባለሦስት-ጥፋት ሕግ“ እያሉ ይጠሩታል። ወንጀለኞች ሦስት ከባድ ወይም ደግሞ አስከፊ ወንጀሎችን የሰሩ ከሆነ ከ25 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት የሚያደርስ ቅጣት ይበየንባቸዋል።

ዘ-ህወሓት በኢትዮጵያ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ላይ ጦርነት አውጇል!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጃዋር መሐመድ ቅኝቶች

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ክንፉ አሰፋ

Jawar Mohamed ጃዋር መሐመድ

መገናኛ ብዙኀንን መቼ እና እንዴት መጠቀም እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ግን እንደ በረሃ ተኩላ እያደፈጠ ይናከሳል። ሲናከስ ደግሞ ማንንም አይምርም። ውለታ የሚባል ነገር አያውቅም። ይሉኝታ አይነካካውም። እፍረትም በእርሱ ዘንድ የለችም። ከቶውን መቀበል እንጂ መስጠትን አያውቅም። አስር ተቀብሎ በዜሮ የሚሸኝ ጀግና ነው። በዚህ ተግባሩ አድናቂው ነኝ። “እኔ-ነኝ” ያለ የዲሲ ፖለቲከኛን ሳይቀር ከአንዴም ሁለቴ እንደማስቲካ እያኘከ መትፋቱን እንመሰክራለን። የጡት አባቱ የሆነው ኦነግንም ቢሆን ‘A Critical Assessment of the Oromo Liberation Front” በሚለው መጣጥፉ እንዳይሆን እንዳይሆን አድርጎ የጠረበ ፍጡር ነው። ይህ ሰው እንደገና ተመልሶ የ"ነፍጠኛውን ሜድያ" ለመጠቀም የማይሞክርበት ምክንያትም የለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ