ከመናቆር መነጋገር ይበጃል (ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም)
ከዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም
Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 5 ቀን 2000 ዓ.ም. March 14,2008)፦ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 29፣ ግለሰቦችም ሆኑ ፕሬስ ወይንም ሌሎች መገናኛ ብዙኀን ሃሳባቸውን በነፃ የመግለጽ ተፈጥሮአዊ መብት ያረጋግጥላቸዋል። የአሜሪካ ሕገ መንግሥት እነዚህን መብቶች ከማረጋገጥ አልፎ እንዲያውም ኮንግሬስ ይህንን መብት ለመገደብ ሕግ ሊያወጣ እንደማይችል ይደነግጋል። ይህ የንግግርና የጽሁፍ ነፃነት ይህን ያህል ዋጋ የሚሰጠው ያለ ፕሬስ ነፃነት ዲሞክራሲና የተመጣጠነ ክብር ያለው ኑሮ ለመኖር የሚያስችል ልማት ፈጽሞ የማይታሰብ በመሆኑ ነው። የፕሬስ ነፃነት መዳበር ወይንም መቀጨጭ አንድ አገር በሥልጣኔ ምን ያህል ወደፊት እንደመጠቀ ወይንም ምን ያህል ወደ ኋላ እንደቀረ የሚጠቁም ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

አሜሪካ ጉድ ፈልቶበታል! አሜሪካ በነቡሹም ቢሆን የታወቀ የነፃነት አገር ነው፤ ይህንን እውነት ሊክዱ የሚዳዳቸው ሰዎች በተለይም አምባ-ገነኖች ሞልተዋል። ነጻነት መንታ መልኮችና ባሕርዮች አሉት፤ በአንድ በኩል በጎና ሰላማዊ፣ ሥራንና ሀብትን ፈጣሪ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ እኩይና ቀጣፊ፣ የሌላውን ሀብት ዘራፊና የወንጀል ፈልፋይ ይሆናል። የነጻነት ባሕርይ ያልገባቸውና ነጻነትን የሚፈሩት እኩዩን የነጻነት ባሕርይ ለማፈን ሲሉ በጎውንም ባሕርዩን አብረው ይከረችሙታል። ምድረ አሜሪካ ሁለቱም የነጻነት ባሕርዮች በገሀድ የሚታዩበት ነው። በአሜሪካ ጉልበትና ገንዘብ ማናቸውንም ነገር የሚያነቃንቁ ኃይሎች ናቸው። እነዚህ ኃይሎች ሕጉን ቢያዶለዱሙትም በትክክል ይሠራል። ጉልበትና ገንዘብ ያላቸው ሁሉ የልማት እንቅስቃሴውን ብቻ ሳይሆን የዜና ማሰራጫዎቹን ሁሉ በቁጥጥራቸው ስር አድርገው የፈለጉትን ፖለቲከኛ የሚያነሡትና ወይም የሚጥሉት እነሱ ናቸው። 


