ምጽዓት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም

በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደኤርምያስ መጣ፡– ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፤ — የእሥራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤- እነሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል፤ በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም፤ ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ነፍስህም እንደምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ በበእኔ ታምነሃልና ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 39/15-18

ኑዛዜ ኤርምያስን አነበብሁ፤ጉድ ነው! አንድ የማውቀውን ነገር አረጋግጥሁ፤ ብዙ የማላውቃቸው ነገሮችን አወቅሁ፤ የማውቀው ነገር ሂሳብ የተማረ ሰው ምን ጊዜም ጭፍን ሎሌ መሆን የማይችል መሆኑን ነው፤ሂሳብ የተማረውን ሰው ለጭፍን ሎሌነት የሚቀጥረው ሰው ግን አንጎሉ የፈረጠ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እስክንድር ነጋ ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ

"ተመስገን፣ ጥሩ ታጋይ እና ሰው ሆኖ ከእስር ይወጣል"
"ተመስገን፣ የህዝብ ልጅ ነው፤ ነገም ከነገወዲያም የህዝብ ልጆች ይፈጠራሉ"

እስክንድር ነጋ "ስለተመስገን ደሳለኝ ሃሳቤን አስተላልፍልኝ" ካለኝ የተወሰደ

ከትናንት በስትያ፣ ሰኞ ዕለት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆነውን አቶ አንዷለም አራጌን በ2007 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ላገኛቸው ችዬ ነበር – ለአቤል አለማየሁ ጋር። ባለፈው ሳምንት የ"ባንዲራ ቀን" በተከበረበት ዕለት ቃሊቲ ከወዳጄ እዩኤል ፍስሐ ጋር ሄጅ እነስክንድርን መጠየቅ ሳንችል ተመልሰን ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ ያለው “የለማኝ መንግስት” አነሳስና አወዳደቅ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም:- ነጻነት ለሀገሬ)

በአሁኑ ጊዜ የረዥም ጊዜ አንባቢዎቼ አንደምያውቁት ሁሉ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ያሉኝን ሀሳቦች እና ማሳመኛ የሙገታ ትንታኔዎች ከፍተኛ በሆነ ግልጽነት፣ እርግጠኝነት እና ለየት ባለ አቀራረብ ሁኔታ በእራሴ ቃላት እና ሀረጎች ለመግለፀ አሞከራለሁ፡፡ በዚህ በአሁኑ ትችቴ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት በአመጽ እና በኃይል ከህዝቦች ፍላጎት ውጭ በስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘውን ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) እየተባለ የሚጠራውን "የለማኝ መንግስት" ገዥ ቡድን የፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍልስፍና መሰረት የሆነውን ጽንሰ ሀሳብ በማስተዋወቅ ውስጣዊ ይዘቱን እና ባህሪያቱን ለመመርመር እሞክራለሁ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

'አሸባሪ ብዕሮች'

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ክንፉ አሰፋ

የፈረንሳዩ አንባገነን ገዥ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአንድ ወቅት ስለ ነጻ ፕሬስ ሲናገር "ከአንድ ሺህ ሻምላዎች ይልቅ አራት ጋዜጦች የበለጠ መፈራት አለባቸው።" ነበር ያለው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወታደራዊ እና አምባገነን ስርአት መገለጫዎች

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ግርማ ሰይፉ  (የፓርላማ አባል)

የወታደራዊ እና/ወይም አንባገነናዊ መንግሰታት መገላጫ በመኖሪያ አካባባያቸው ይገለፅ እንደሆን በሚል፡፡ ከዚህ ቀጥዬ የማነሳቸውን የወታደር መኖሪያዎች እና የቤተ መንግሰት ሁኔታን ይመለከታል፡፡ ዘወትር እነዚህን ግቢዎች ባየኋቸው ቁጥር የሚመጣብኝ አሳብም ስለሆነ ነው፡፡ ለነገሩ የዚህ ዓይነት አስተሳሰብ አዲስ አይደለም፡፡ የኢኮኖሚክስ ትምህርት መጀመሪያ የሆነው አንድ በላተኛ፣ አንድ አቅራቢ፣ አንድ ገበያ የሆነው ከአንድ ሰው ጀምሮ፣ ወደ ቤተሰብ እና ሀገር የሚያድገው ሞዴል ተፅህኖሞ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገሮችን ከቀላል በመነሳት ወደ ውስብሰብ ደረጃ ለማጥናት ይረዳል የሚል እምነትም አለኝ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የደርግና የወያኔ የውይይት ክበብ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አንተነህ መርዕድ

ላለፉት አርባ አመታት በአምባገነኖች መዳፍና በካድሬዎች ቁጥጥር ስር ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘላቂ ነፃነት እስካላገኘ ድረስ የስርዓት መቀየር ብቻ ለነፃነቱ ዋስትና አልሆነውም፤ አይሆነውምም። አምባገነኖች ጉልበቱን ከመበዝበዝ፣ ከማሰርና ከመግደል አልፎ ስብዕናውን በመግፈፍ የጎደፈ አስተሳሰባቸውንና ፍልስፍናቸውን በዜጎች አዕምሮ በመሙላት አገዛዛቸውን ዘላቂ ያደረጉ ይመስላቸዋል። የሚገርመው ደርግ ሆነ ወያኔ የህዝብ መሰረት ሲያጡ፣ ዙርያ ገባው ገደል ሲሆንባቸው፤ በካድሬዎቻቸው ህዝቡን ሰብስቦ በፕሮፓጋንዳቸው ማጥመቅ  ልትበጠስ የደረሰችውን በስልጣን ዘመን የሚያራዝምላቸው ይመስላቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ