የመለስ "ትሩፋቶች" - መጽሃፍ ቅኝት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ክንፉ አሰፋ

ደራሲ - ኤርምያስ ለገሰ

ብዛት - 406 ገጾች

አሳታሚ - ነጻነት አሳታሚ ድርጅት

እንደ መንደርደርያ

በስፋት ሲወራለት የነበረውን ይህን መጽሃፍ ሙኒክ-ጀርመን ላይ ገዝቼ ለማንበብ እያፈላለግኩ ሳለሁ፤ አንድ ወዳጄ ይዞት አየሁ። የደበዘዘ የመለስ ፎቶ ያለበትን ይህንን መጽሃፍ የኦስሎው አበበ እጅ ላይ ነበር። ገና ሰላምታ ሳንለዋወጥ ነበር መጽሃፉን ከእጁ ላይ የነጠቅኩት። ታማኝ በየነም እዚያው አብሮን ስለነበር አስተያየቱን ጣል አደረገ። "መነበብ ያለበት መጽሃፍ" እንደሆነ አበክሮ ነገረኝ። ታማኝ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ መጻህፍት በሙሉ እንደማያመልጡት አውቃለሁ። በዚህ አዲስ መጽሃፍ ላይ አንዳች አዲስ ነገር እንደሚኖር ከንግግሩ ለመረዳት አያዳግትም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብሄራዊ መግባባት ወይስ አገራዊ ውህደት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም

አንዳንድ እንደዘረኝነት፣ ጐሰኝነትና የሃይማኖት ጥላቻ ስለመሳሰሉ አጸያፊ ክስተቶችና ሕዝባዊ ግንኙነቶች ማንሳትና ስለእነርሱም መጻፍ የሚቀፍ ከመሆኑም በላይ፤ ያልሆነ ስም ሊያሰጥና በዘረኝነት ተጠቃሚ የሆኑ አካላትንም ሊያስከፋ ይችላል። ሆኖም ሳይመሽ አገርን ከውድቀት ለመታደግ እና ሕዝብን ከጥፋት አፋፍ ለመመለስ ሲባል፤ ከአገርና ከሕዝብ የሚበልጥ የለምና ይሉኝታን ዋጥ አድርጐ በፍርሃት ሳይገደቡ፣ በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ሳይሽሞነሞኑ እነዚህን አገር በታኝ ክስተቶችን በአደባባይ አፍርጦ ለማውጣት ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ሰው መሆንም በቂ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አበሻና ጽሕፈት

የአንባብያን ድምፅ: 3 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar InactiveStar Inactive

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

በቅርቡ ከአንድ ወዳጄ ጋር ስለኢየሩሳሌም ማኅበር ስናወራ መሥራቹ አቶ መኮንን ዘውዴ ትዝ አሉኝና ስለሳቸው ውለታ ሳወራ ነበር፤ ከሳቸው ጋር ተያይዞም ከዚህ በፊት አይ አበሻ! በሚል አጠቃላይ ርእስ አበሻና ልመና ወዘተ. እያልሁ መጻፍ ጀምሬ የነበረው ትዝ አለኝ፤ አንዳንድ ስላልገባቸው ነገር ሁሉ መጻፍ የሚወዱ ሰዎች አቅጣጫውን ሊለውጡት ሙከራ ሲጀምሩ ትቼው ነበር፤ አሁን የመክሸፍን ጉዳይ ደግሜ ለመጻፍ ስጀምር አንዳንድ በጣም መሠረታዊ የሆኑ የመክሸፍ መገለጫዎችን ስጽፍ በመጽሐፍ መልክ እስኪወጣ አላስችል አለኝና አንዱን ሀሳብ አደባባይ ለማውጣት ወሰንሁ፤ በዚያውም አቶ መኮንን ዘውዴን ማስታወሻ ይሆነኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነ ህሊና መቼ አባታቸውን ያገኛሉ?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዳዊት ሰለሞን

ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣን ዛሬ አነበብኳት። የጋዜጣዋ ባልደረባ የሆነው በላይ ማናዬ በቅርቡ ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው የሺዋስ አሰፋ ቤት ተገኝተው የየሺዋስን ሁለት ህጻናት ልጆች ማግኘታቸውንና ህጻናቱም ስለ አባታቸው የሚያስቡትን እንደነገሩት ይተርካል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ ቆርጦ መቀጠልም ተሳናት!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ሳምሶን አስፋው - አውስትራሊያ

የአቶ አንዳርጋቸው ቃልና የወያኔ ፕሮፓጋንዳ

ሰሞኑን በወያኔ መንግስት የፖሊስ ፕሮግራም የቀረበው “አቶ አንዳርጋቸው ለመንግስት ጠቃሚ መረጃ ሰጡ” የሚለው ዜና ኢትዮጵያዊውን ሁሉ እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ነው። የዜናው አነጋጋሪነት የሚነሳው ለዜናው አብይ ግብአት እንዲሆን፤ በወጉም ሳይታሰብበት ተለጣጥፎ የቀረበው የቪዲዮ ክሊፕ የዜናውን ጩኸት አለማስተጋባቱ ነው። በመጀመሪያ የምናነሳው ጥያቄ የወያኔ ባለስልጣናት ይህንን በተራ ግለሰብ እንኳ ቢቀርብ የሚያሳፍር ደካማ የማስመሰል ስራ በመንግስት ደረጃ ለማቅረብ ያስገደዳቸው ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ይመስለኛል። ለዚህ ደግሞ የተለያዩ መላምቶችን መሰንዘር እንችላለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፖለቲካና ግለሰብ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

ለእኔ ፖሊቲካና የግለሰብ ጠባይ እንደውሃና ዘይት የማይደባለቁ ነገሮች ይመስሉኛል፤ አጼ ምኒልክ ‹‹አመልህን በጉያህ›› ያሉት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፤ ዘይትና ውሀ በባሕርያቸው የሚለዩትን ያህል ፖሊቲካና ግለሰብም የባሕርይ ልዩነት አላቸው ማለት ነው፤ የወያኔ መሪዎች ምንም ነገር የማይሰምርላቸው፣ ከመጀመሪያውኑ እነዚህን ሁለት የማይደባለቁ ባሕርዮች አደባልቀው በመንሣታቸው ነው፤ ፖሊቲካ ለማኅበረሰቡ መቆርቆር ነው፤ ለሕዝቡ መቆርቆር ነው፤ ለአገር መቆርቆር ነው፤ የፖሊቲካ መነሻም ይኸው መሆን አለበት፤ ዓላማውም የማኅበረሰቡ፣ የሕዝቡ ልማት እንጂ ጥፋት አይደለም፤ የነበረውንና ያለውን ማጥፋት የፖሊቲካ ዓላማ ሊሆን አይችልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ