ደራሲ:- ኤርምያስ ለገሰ
ቅኝት:- መስፍን ማሞ ተሰማ

መንደርደሪያ
በድሮ ዘመን የኖሩ እንስሳት እንዲህ ዘመሩ።
የእንግሊዝ አራዊት፤
የአየርላንድ አራዊት፤
የየሀገሩ ሁሉ አራዊት፤
ተሳተፉ የደስታዬን ምንጩን፤
ስለመጪው ብሩህ ዘመን!
ይዘገያል ወይ ይፈጥናል፤
ያ! ቀን ግን ይመጣል፤
ጨቋኙ ሰው ይገረሰሳል! . . . ዘምረው ዝም አላሉም። ዘምረው አመፁ። አብዮት አፈነዱ፤ የእንስሳት አብዮት። በሚኖሩበት ሀገር - በእነሱ አጠራር፤ የእርሻ ጣቢያ - ለዘመናት በጭቆና ቀንበር ረግጦ ሲገዛቸውና ሲመዘብራቸው በኖረው የሰው ዘር ገዢያቸውና ግብረ አበሮቹ ላይ ሆ! ብለው ተነሱ። ቀንበር በቃን። ባርነት በቃን። ብዝበዛ በቃን። … ነፃነት እንጂ። 

እነሆ አብዮቱ ድል ነሳ። ገዢያቸውና አበሮቹ ሸማና ነፍሳቸውን ይዘው ሸሹ፤ ተሰደዱ። የእርሻው ጣቢያም - ሀገራቸው የእንስሳቱ - የነሱ ሆነ። ስለ አብዮቱ የሰበኩት፤ የቀሰቀሱትና ያስተማሩት አሳሞች አስተዳደሩን ተረከቡ፤ ከነመዋቅሩ። እናም የእንስሳቱ ሀገር - የእርሻ ጣቢያው - መንግሥት ሆኑ። አሳሞች ብቻ የሚመሩት መንግሥት። (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ