ከነጻነት ታጋዮች ጋር በቂሊንጦ

ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው ‹‹ጥቁር ሳምንት›› (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) መካሄዱ ይታወሳል። በዚያ የጥቁር ሳምንት ዘመቻ ወቅት በመጨረሻው ቀን አስተባባሪዎቹ አዲስ አመትን በማስመልከት ‹አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር› በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮች እንዲጠየቁ ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም። በመሆኑም የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በቂሊንጦ የሚገኙ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላትንና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በመጠየቅ የዘመቻውን አካል አከናውነዋል። ቀጥሎም የጥቂት እስረኞችን መልዕክት በአጭር በአጭሩ አቅርበናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማለዳ ወግ… በ2006 ዓ.ም የመጨረሻ ሰዓታት፣ የማይረሱኝ የተጨመቁ ትዝታዎች

ነቢዩ ሲራክ

አዲስ የነበረውና ዛሬ ገና 12 ወር ከ5 ቀኑ “ያረጀ ያፈጀ ” የምንለው 2006 ዓ.ም ለመገባደድ ጥቂት ሰአታት ብቻ ነው የቀሩት። 2006 ዓ.ም በሳውዲ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያን ልዩ የማይጠፉ ትዝታዎቸን አስተናግደንበታል።

* ፍጹም የማይረሱኝ ትዝታዎች …
በ2006 ተከስተው የማይረሱኝ የተለያዩ ክስተቶች እና አስደሳችና መራራ ትዝታዎች ብዙ ቢሆኑም የተጨመቁትንና ፍጹም ከአዕምሮየ የማይጠፉት በአዲሱ አመት መግቢያና በአሮጌው አመት መሸኛ የመጨረሻ ሰአታት ላድታውሳቸው ግድ አለኝ …

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን “የስጋት” መስመር (ከዞን9 ጦማሪያን)

ይህ አመት አንደተለመደው አይነት አመት ቢሆን ኖሮ በዚህ ወቅት የዞን9 ጦማርያን በጦማሪት ማህሌት አስተባባሪነት፣ በአጥናፍ ብርሃኔ እና በጆማኔክስ ካሳዬ ትብብር የአመቱን ታላላቅ ክስተቶች አሰባስበው ከመታተሙ በፊት ለቡድኑ ክለሳ የሚያቀርቡበትና የተረሱ እና ለክስተትነት የማይበቁ የምንላቸውን ሁነቶች የምንለይበትና የአመቱን የጊዜ መስመር የምናወጣበት ወቅት ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብርሃኑ ተዘራና አብዱ ኪያር ካልጋሪን በፍቅር አደመቋት (ሄርሜላ አበበ)

በምዕራብ ካናዳ ኑሯቸውን ያደረጉ ኢትዮጵያውያን በካልጋሪ ከተማ ያደርጉት የእግር ኳስ ፈስቲቫል እሁድ ኦገስት 31 ምሽት ተጠናቀቀ። በዚሁ ውድድር ላይ ከተለያዩ ከተሞች የመጡ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉ ሲሆን ኤድመንተን ቫንኮቨር ዊኒፔግና ካልጋሪ ከባድ ፉክክር አሳይተው በቫንኮቨር አሸናፊነት ውድድሩ ተጠናቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ጥቁሩን ሳምንት ተቀላቀሉ” መልእክት ከእስክንድር ነጋ

እንደሰማሁት ከሆነ ጥቁር ሳምንት በሚል የተጀመረው ዘመቻ ጥሩ ዘመቻ ነው፡፡ በማህራዊ ሚዲያው ሲንቀሳቀሱ የነበሩትም ሆነ ጋዜጠኞች በመታሰራቸው እንቅስቃሴው አለመዳከሙ ያስደስታል፡፡ መጭው ዘመን የነጻነት ይሆን ዘንድ ኢትዮጵያውያን ይህን የመሰሉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ፣ ማበረታታትና መቀላቀል አለባቸው፡፡ በተለይ በአሁኑ ዘመን ማህበራዊ ሚዲያው ትልቅ ለውጥ እያመጣ ነው፡፡ በግብጽና ቱኒዚያ ማህበራዊ ሚዲያው ቀላል የማይባል ለውጥ አምጥቷል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔና ይሉኝታ አይተዋወቁም

ጋዜጠኛ አንተነህ መርዕድ

ህወሃት በሻዕብያ ታዝሎ* ምኒልክ ቤተመንግስት ከገባና ኦነግንም ሆነ ሌሎቹን ጠፍጥፎ የሰራቸውን መናኛ ድርጅቶች እንኳ ሳያስቀርብ በብቻው የተያያዘው ዘረፋ፣ ሁሉን ለእኔ ብቻ ያለ ሂደቱ ያላስደነገጠው ኢትዮጵያዊ አልነበረም። ያለፉትን ስርዓቶች የተሻገሩ ሁለት አንጋፋ ጓደኛም ጋዜጠኞች ሲጨዋወቱ በቦታው ነበርሁ። አንደኛው ወያኔ ነፃ አወጣዋለሁ ከሚለው ከኩሩው ኢትዮጵያዊ ከትግራይ ህዝብ አብራክ የተገኘ ነበርና "ወንድሜ ይሉኝታ በትግርኛ ምንድን ነው የሚባለው?" ሲል ጠየቀው። "ይሉኝታ..ይሉኝታ..." እያለ ቃሉን ማፈላለግ ሲጀምርና ፈጥኖም ቃሉን ማግኘት ሲሳነው "ተወው ወንድሜ የሌለውን ነው የጠየቅሁህ ቃሉ ከሌለ ወያኔዎች ከየት ይማሩታል ብዬ ልጠብቅ" በማለት ሁላችንንም አሳቀን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከታሳሪ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪና አህመዲን ጀበል ጋር በቂሊንጦ የነበረኝ ቆያታ

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ
"እኛ ታስረንም፣ በኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት እና ጋዜጠኞች ላይ የሆነው ነገር እጅግ ቅስም ይሰብራል (It's really heart breaking!)" ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ
"እስር ደግም ነገር ነው" ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ
"የነጻነት ትግል ላይ እንዳለሁ ያወኩት እስር ቤት ነው" ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ
"መጽሔቶች መታተም መቆማቸው ያሳዝናል፣ አማራጩ ምን ይሆን?" አህመዲን ጀበል (የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል)

ከትናንት በስትያ፣ ሰኞ ነሐሴ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በጣም የናፈቁኝን ታሳሪ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ለመጠየቅ በማቀድ፣ ረፋድ ላይ ወደቂሊንጦ እስር ቤት አመራሁ። በቃሊቲ ወህኒ ቤት ዋና በር ጋር በታክሲ ሳልፍ፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እና ኤዶምን ካሳዬ፣ ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁንን፣ አቶ አንዷለም አራጌን፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና ሌሎች የማውቃቸውን እስረኞች በሀሳቤ መጥተው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊነት . . . ( ክፍል ፪ )

አንዱዓለም ተፈራ (የእስከመቼ አዘጋጅ)

ባለፈው ጽሑፌ ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ፤ ከልቤ ያማምንበትን በጥቅሉ አስፍሬ ነበር። በዚያ፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ ማለት፤ ታሪካቸውን፣ ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውን፣ መላ የኑሮ ሁኔታቸውን ጨምሮ ማለት ነው። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአሜሪካ እሴቶች በአፍሪካ ውስጥ ምን ፋይዳ አላቸው?

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

“እኛ ትክክለኛ እና ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ነገሮችን አከናውነናል፣ ሆኖም ግን ከዚህ በተለዬ መልኩም ህዝብን አሰቃይተናል፣ ከእሴቶቻችን ጋር ተጻጻሪ የሆኑ ነገሮችን ፈጽመናል። ከፍ ወዳሉ የምርመራ ስልቶች ስንገባ ማለትም ማሰቃየትን ጨምሮ ማንም ሚዛናዊ የሆነ አስተሳሰብ ያለው ሰው እንደሚያስበው እና እንደሚያምነው የምናደርገው ድርጊት ማሰቃየት ሆኖ ሲገኝ መስመሩን አለፍን ማለት ነው። እናም ይህ ጉዳይ ግንዛቤ ሊወሰድበት እና ተቀባይነትንም ማግኘት አለበት“ በማለት ፕሬዚዳንት ኦባማ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጸዋል። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊነት ማለት

አንዱዓለም ተፈራ (እስከመቼ) 

“ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው።”

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ