Dr. Gashawዓለማየሁ ታዬ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

በያዝነው ዓመት የአማርኛ ቋንቋን የሥነ ግጥም እልፍኝ ካደመቋት አዳዲስ መድበሎች መካከል “ስንኞች ከባህር ማዶ” እጄ ገብታለች። በአንድ መቶ ሦስት ገጾች ተደጉሳ የሕትመት ብርሃን የሞቀችው ይህች መድበል 72 የአማርኛ እና ስምንት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ግጥሞችን ይዛለች። ገጣሚው በመግቢያው እንዳብራራው ግጥሞቹ የተጻፉት ባለፉት 38 ዓመታት ነው።

 

የስደት ሕይወት፣ የሀገር ናፍቆት፣ የሠላምና የፍትህ ጥሪ፣ ጀግና ኅልፈቱ፣ የእናት ፍቅር፣ … ወዘተ የግጥሞቹ ጭብጦች መሆናቸውንም ገጣሚው አውስቷል። ዶ/ር ጋሻው ትኩረት የሰጠባቸውንና የተለየ ጣዕም የታየባቸውን ግጥሞች እነሆ በዚህ የመጽሐፍ ሂስ ለመዲሰስ ተሞክሯል።

 

ከቅርብ ግዜ ወዲህ በአገራችን የስነ-ግጥም ሕትመት ባህል በጉልህ የሚታይ ክስተት ቢኖር በባህር ማድ የሚኖሩ ሃበሾች የግጥም ስራዎቻቸውን ለሕትመት ማብቃታቸውና ያገራችንን ግጥም በተለየ አቀራረብ ማድመቃቸው ነው። እነዚህ በባህር ማድ የሚኖሩ ገጣምያን በስደት ሕህወት መራራነትና በአገር ቤት ትዝታና በወገን ናፍቆት ጭብጦች ዙሪያ አበርክተው መጻፋቸውም እሙን ነው። በዚሁ ተርታ ከሚመደቡት ገጣምያን አንዱ የሆነው ዶ/ር ጋሻው፤ “ይህም ሀገር ሆኖ” በሚል ርዕስ የስደት ሕይወትን ጣዕም አልባነት መረር ባለና ቁጭት በጉልህ በሚታይበት ድምጸት እንደሚከተለው ከትቦታል። ጥቂት ስንኞች፤ … (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤ.ፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ