"የሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ግድያና ጥቃት የተፈጸመው በኦርቶዶክሳውያን ላይ ነው" የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

የልጃችን የሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ እና ግድያውን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ ዞኖች ተቀነባብረው በተፈጸሙ ጥቃቶች የተጎዱ ኦርቶዶክሳውያንን መርዳትንና መልሶ ማቋቋምን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

“አማን አማን እብለክሙ ከመ ትበክዩ ወትላህዉ አንትሙ፤ ወዓለምሰ ይትፌሣሕ፤ ወአንትሙሰ ተኃዝኑ፤ ወኃዘንክሙ ፍሥሐ ይከውነክሙ" እውነት እውነት እላችኋለኹ፤ እናንተ ታለቅሳላችኹ፤ ሙሾም ታወጣላችኹ፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችኹ፤ ነገር ግን ኃዘናችኹ ወደ ደስታ ይለወጣል።” (ዮሐ.16፥20)

ሐጫሉ ሁንዴሳ ስመ ጥምቀቱ ኃይለ ገብርኤል፣ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት በአዲስ አበባ መገደሉ ይታወሳል። ቤተ ክርስቲያን፥ በዚያድንገተኛ የልጇ ግድያ ከባድ ኃዘን ተሰምቷታል። ኾኖም፣ በግድያው የተሰማትን ኃዘን ለመወጣት ጊዜ ሳይሰጣት፣ ኃዘንተኛነቷ ተረስቶ እናእንደ ጠላት ተቆጥራ፣ በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች በክርስቲያን ልጆቿ ላይ ዘግናኝ ፍጅት እና መከራ ተፈጸመባቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መንግሥት የአገሪቱን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ብቻውን የመፍታት አቅም የለውም!

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive
የአብሮነት መግለጫ

ከአብሮነት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት (#አብሮነት) የተሰጠ መግለጫ

አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት (አብሮነት) ባለፉት ጊዜያት የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታዎች እየተከታተለ እና እየገመገመ አቅጣጫ የሚያሳዩ መግለጫዎችን ሲያወጣ መቆየቱ ይታወሳል። አብሮነት በነዛ ሁሉ ጊዜያት የለውጥ ሒደቱ ሃዲዱን እየሳተ መሆኑን እና አገራችን የሕልውና አደጋ ውስጥ ከመውደቋ በፊት ተጨባጭ የመፍትሔ እርምጃዎች እንዲወሰዱ አማራጭ መፍትሔ ጭምር በማስቀመጥ ሲወተውት ቆይቷል። ነገር ግን የለውጥ ኃይል ነኝ ባዩ መንግሥት ከኔ ውጭ መፍትሔ ላሳር፤ የማሻግራችሁም እኔ ብቻ ነኝ በሚል መታበይ የቁልቁለት ጉዞን መርጧል። በዚህ የመንግሥት ፍጽም የሆነ አንባገነናዊ ባሕርይም የተነሳ አገራችን አሁን የምትገኝበት ሁኔታ ለውጡ ከመምጣቱ በፊት ከነበረው ሁኔታ ጋር እጅግ ተመሳሳይ ነው። ከዚህም የከፋ የሕልውና አደጋ ተጋርጦብናል። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግሥት ሕግና ስርዓትን ማስፈን እየተሳነው በየአካባቢው ንጹኀን ኢትዮጵያዊያን ማንነትን እና ኃይማኖትን ማዕከል ባደረገ ጥቃት ሕይወታቸውን እያጡ ነው፣ አካላቸው እየጎደለ ነው፣ ጥሪታቸውን አሟጠው ያፈሩት ሀብትና ንብረት እየወደመ ነው። በአገር ውስጥና በአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘር ጭፍጨፋ/ጄኖሳይድ ነው ብለው በገለፁት በዚህ አሰቃቂ ድርጊት ዜጎች ተንቀሳቅሶ ሀብትና ንብረት የማፍራት ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው አደጋ ላይ ወድቋል። የዜጎች ለዘመናት የተገነባው የመቻቻል፣ የመከባበር፣ የመተዛዘን አኩሪ ባህላችን እየተደፈቀ ዘረኝነት፣ ጎጠኝነትና መንደርተኝነት ከምንግዜውም በላይ ነግሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሕወሓት ቀቢጸ ተስፋ የተጠናወተው የትግል ስልት ለምንና ለማን?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Amhara Region Prosperity Party

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ

ለትግራይ ሕዝብ ሲባል ሕወሓትን ያቀፈ የትግል ስልት መከተል ሆደ-ሰፊነት እንጂ ድንቁርና አይደለም። እስከአሁን በነበረው የትግል ጉዞ ሕወሓትን ከልክ በላይ መታገስ መስተዋሉ ተገቢና ትክክለኛ አቅጣጫ ነው። አሁንም ቢሆን ለትግራይ ሕዝብ ያልተመቸ ምንም አይነት ሁኔታ መከተል አያስፈልግም። የትግራይ ሕዝብና ሕወሓት በፍጹም አንድ አይደሉም፤ አንድ ሆነውም አያውቁም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለሰላማዊና ሕጋዊ ትግል ያለን ታማኝነት በሐሰት ውንጀላ አይገታም!! - ባልደራስ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
ባልደራስ

ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ሕዝብ በተባበረ ትግል ጨቋኝ፣ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ-ዴሞክራሲ የነበረውን የሕወሓት/ኢሕአዴግ አገዛዝ አስወግዶ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሰፍን መጠነ ሰፊ ትግል ማድረጉ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ በዶ/ር ዐቢይ የሚመራው የኦዴፓ/ብልጽግና አመራር የሕዝቡን የለውጥ ፍላጎት ከዳር ለማድረስ በአደባባይ ቃል ገብቶ ኃላፊነቱን መረከቡም ይታወሳል። ኾኖም ይህንን ወደ ነፃነትና ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ የሽግግር ጥያቄ በተገቢው ሁኔታ ለመመለስ በጣም አቅቶታል። ላለፉት ሁለት ዓመታት በገሀድ እንደታየው የብልጽግና ፓርቲ እየተከተለ ያለው ፖለቲካ በተረኝነት መንፈስ የተቃኘ ነው። ለዚህም ነው ፓርቲው የኢትዮጵያን ፖለቲካ ማረጋጋትና፣ የሕዝቡን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበርና ብሔራዊ መግባባት ለማስፈን ያቃተው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ያለበቂ ውይይት እና ግልጽነት በጎደለው መልኩ የኢትዮ ቴሌኮምን ከፊል ድርሻ ለመሸጥ እሄደበት ያለው ጥድፊያ በአስቸኳይ ይቁም! (ኢዜማ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
ኢዜማ

ገዢው ፓርቲ ያለበቂ ውይይት እና ግልጽነት በጎደለው መልኩ የኢትዮ ቴሌኮምን ከፊል ድርሻ ለመሸጥ እሄደበት ያለው ጥድፊያ በአስቸኳይ ይቁም!

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ

አንኳር

- ቴልኮም በ21ኛው ክፈለ ዘመን የፋይናንስ ሥርዓት መተግበሪያ፣ የመገናኛ ብዙኃን የደም ቧንቧ፣ ከፍተኛ የሆነ አገራዊና ወታደራዊ መረጃዎችን ማስተላለፍያ፣ ከመሪዎች ጀምሮ ከፍተኛ የአገር አስተዳደሪዎች መረጃ መቀባበያ፣ ለደህንነት ሥራዎች መረጃ ማግኛ ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የጦር መሳሪያና ጦር ሜዳ ሆኖ ተመልከተናል። ከዚህ ባለፈ ኢንዱስቲሪው ብዙ ሌሎች ኢኮኖሚ ዘርፎች ተወዳደሪነታቸውን ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆነ ግብዓት እና ለአገራችን የወደፊት እድገት ያለውን አቅም መገነዝበ ተገቢ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ