Sebhat Gebregziabher”ሶቅራጥስ ፈላስፋ ነው። ሚስቱ ደግሞ ጨቅጫቃ ነች። አንዳንዴ ወይዘሮ ይሉኝታና አቶ ይሉኝታ ቢስ ይጋባሉ። ሶቅራጥስ ሲፈላሰፍ ነው የሚውለው። ትዳርዋን ለምትወድ ሴት ደግሞ ይህ ዓይነቱ አካሄድ የሚጥም ሕይወት አይደለም። የሶቅራጥስ ሚስት ሲበዛ ጨቅጫቃ ነበረች።

”ታዲያ ሶቅራጥስን ደቀ መዛሙርቱ ስለትዳር ጠይቀውት ሲመልስ ”ትዳር መመሥረት ጥሩ ነው። ዝምተኛና ሰላማዊ ሚስት ካጋጠመችህ ደስተኛ ሕይወት ትኖራለህ። ከጨቅጫቃዋ ጋር ሕይወት ካቆራኘችህ ደግሞ ፈላስፋ ትሆናልህ” አላቸው። እኔም ሁለተኛው ትዳሬ ፈላስፋ አድርጎኛል።”

መጽሐፍ ርዕስ፣ ”ማስታወሻ”
ደራሲ፣ ዘነበ ወላ
ከገጽ ፳፫ የተወሰደ ሲሆን፣ ይህን ምላሽ የሰጠው ደራሲ ዘነበ ወላ ስለሁለተኛ ትዳሩ ሲጠይቀው ነበር።
ዕትም፣ ስብኃት ገብረእግዚአብሔር ከዚህ ዓለም ከተለየ በኋላ ፳፻፮ ዓ.ም. የታተመው

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!