በአውስትራሊያ ሜልበርን በየዓመቱ የሚደረገውን የስፖርት ውድድር ምክንያት በማድረግ የምትዘጋጀው "ኢትዮ-ቶርናመንት" መጽሔት ለንባብ በቅታለች። "ኢትዮ-ቶርናመንት" ዓመታዊ መጽሔት በዚህ ዕትሟ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ግዙፍ ሚና የተጫወቱ እንግዶችን ይዛ ቀርባለች።

 

አቶ ካሣ ገብረጊዮርጊስ - ለ17 ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ፣ አቶ ጌታቸው ተስፋዬ - የወቅቱ ኢ.ኤስ.ኤፍ.ኤን.ኤ ፕሬዘዳንት፣ ሰሎሞን መኮንን ሉቾ - ለረዥም ዓመታት የብሔራዊ እግር ኳስ ቡድናችን ኮከብ ተጫዋች እና ክብሮም ተ/መድህን - ለረዥም ዓመታት የብሔራዊ እግር ኳስ ቡድናችን ኮከብ ተጫዋች (አሁን ኤርትራዊ) ጋብዛለች። ሌሎችም ዝግጅቶችን አካታለች። (ሙሉውን መጽሔት ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!