ጌታቸው ረዳ

የሕወሓቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ ጌታቸው ረዳ

“ከሁሉም ነገር በላይ ግን ትግራዋይ እየተሸነፍኩ ነው የሚል እሳቤ ለአማራ ሊጠረጥርና ሊያጎነብስ፣ ለኦሮሞ ሊጠረጥርና ሊያጎነበስ፣ እንደ ሕዝብ ለሶማሌ ሊጠረጥርና ሊያጎነብስ ነውር ነው! ይህ በትግራዋይ ታሪክ አልነበረም!!

“ከሁሉም በላይ ደግሞ ትግራዋይ መበለጥን አይፈልግም። ልማት የሚፈልግና የሚያከብር ትግራዋይ ያ ትክክለኛ ትግራዋይ ነው። በራሳችን ድክመት አደጋ ላይ የወደቀውን ትግራዋይ ግን ልናድነው ኃላፊነት አለብን!

የሕወሓቱ ከፍትኛ ባለሥልጣን ጌታቸው ረዳ ሰሞኑን በጀርመን ፍራንክፈት በተካሄደው በምስጢር ትግሬዎች በተሰበሰቡበት ስብሰባ ላይ ከተናገራቸው ውስጥ፡-

- ጥቃቶች በየቦታው እየተካሄዱ ነው ያሉት። ስለዚህ ይህንንም ማስቀም አለብን።

- ጥቃቶችን ካስቆም በኋላ መመታት ያለበትን መምታት፤ ሊባረረ የሚገባውን ማባረር፤ ገለል ሊል የሚገባውን ገለል በማደረግ “አገራችንን” [ትግራይን ማለቱ መሆን አለበት] መለወጥ መቻል አለብን።

- ይህ የእኛ ብቻ ሀብት ነው፤ ለእኛ ብቻ ይገባናል የሚባል ነገር የለም። ኢትዮጵያ የእኛም የሁላችንም ናት።

- ከሁሉ በላይ ልነግራችሁ የምፈልገው TPLF የራሳችን የሆነ መስመር እስከያዝን ድረስ አሁንም ደግሞ መስመሬን ይዤ እቀጥላለሁ ነው ያለው።

- እኔ ዛሬ ብዙ መናገር አልፈልግም። ይህ የሕልውናችን ጉዳይ ነው።

- ኢሕአፓ፣ ኦነግ የሚባሉ ሁሉም የተለያዩ ድርጅቶች እዚያው ነበሩ። በዚያን ግዜ ጠላት አድርገው የሚወስዱት ግን የትግራይን ሕዝብ ነው። ትግራዋይ ለምን?

- አትጨነቁ፣ ምንም የሚያስጨነቅ ነገር የለውም። የትግራይ ሕዝብ ሥርዓት የቀየረ እነዚህን ኃይሎች ደግፎና መሪ ሆኖ ስለመጣ ነው አሁን ይህ ሁሉ ጫጫታ። ሊያንበረክክቱ ይፈልጋሉ።

- ትግራዋይ ወጥተው እንደዚህ ያደርጋሉ ይባባል። እነሱ ናቸው ፎቆችን የሚሠሩት ይባላል። ብዙ አልሠራንም። እነሱ ግን ይሠሩበት ነበር። በኋላ መስመራችን ቀይረን ወደ ሕዝብ መግባት የጀመርንበት ሰዓት አሁን ነው። ድንገት እየተወያየን አሁን ነው ወደ ሕዝቡ መግባት የጀመርነው። እዩት ስንፍናችን!!

- እንድስማማ ኢሕአዴግም እንደ ኢሕአዴግ Responsibility ወይም ተጠያቂነት ይወስዳል። በዚህም ተስማምተናል። ይህ ነገር ሲፈጠር ሕወሓት አስቀድሞ ተስማምቶበታል። ሌሎችም ተስማምተውበታል።

- በዚህ ቅርብ ግዜ የተባለውን ልንገራችሁ። የትግራይ የበላይነት የሚባለውን ነገር እንዲቀር ሕወሓት አንዳንድ ነገሮችን ማድረግ አለበት ተባለ። እኛ ጠርተን ስለመጣን በዝርዝር ነገር ላይ ብቻ ካወራን discuss ስናደርግ ይህ ንግግር ከዚህ ከኢሕአዴግ መምጣት የለበትም አልን። እኛ ነው የዘራነው። ስለዚህ እኛ እራሳችን እንታገለዋለን ብለው እራሳቸው መንቀሳቀስ ጀምረዋል። ይሳካል ወይም አይሳካም በአንድ ላይ ሆነን የምናየው ይሆናል። ከሁሉም በላይ ግን መሳካት መቻል አለበት! ይህ ሁኔታ መቀየር መቻል አለበት! ሁላችንም አንድ ሆነን መንቀሳቀስ መቻል አለብን።

- ከሁሉም ነገር በላይ ግን ትግራዋይ እየተሸነፍኩ ነው የሚል እሳቤ ለአማራ ሊጠረጥርና ሊያጎነብስ፣ ለኦሮሞ ሊጠረጥርና ሊያጎነብስ፣ እንደ ሕዝብ ለሶማሌ ሊጠረጥርና ሊያጎነብስ ነውር ነው! ይህ በትግራዋይ ታሪክ አልነበረም!!

- ከሁሉም በላይ ደግሞ ትግራዋይ መበለጥን አይፈልግም። ልማት የሚፈልግና የሚያከብር ትግራዋይ ያ ትክክለኛ ትግራዋይ ነው። በራሳችን ድክመት አደጋ ላይ የወደቀውን ትግራዋይ ግን ልናድነው ኃላፊነት አለብን! …

የሕወሓቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ ጌታቸው ረዳ

በጀርመን ፍራንክፈት በተካሄደው ምስጢራዊ የትግሬዎች ስብሰባ ላይ አቶ ጌታቸው ረዳ የተናገሩትን ከዚህ በታች የማዳመጫ ቁልቁን በመጫን ያድምጡ።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!