Zone9 bloggers

(ዞን፱) የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድቤት መዝገቡን መርምሮ እንዳልጨረሰ በመግለጽ ለታህሳስ 21 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አምስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች፣ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ በፍቃዱ ኃይሉ (ከእስር ቤት)፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ አቤል ዋበላና ናትናኤል ፈለቀ ዛሬ ማክሰኞ ኅዳር 27፣ 2009 ለመጨረሻ የይግባኝ ብይን ይቀርባሉ ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም፤ ፍርድ ቤቱ እንደተለመደው አሁን አራዝሞታል።

ሰባት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችና ሦስት ጋዜጠኞች ከታሰሩበት ሚያዚያ 17፣ 2006 ጀምሮ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት እየቀረቡ ቆይተው አምስት ተከሳሾች ከሳሽ የፌደራል ዓቃቤ ሕግ ያቀረበውን ክስ አንስቻለሁ በማለቱ ሐምሌ 01፣ 2007 የተፈቱ ሲሆን፣ አራቱ ተከሳሾች ደግሞ ነፃ ናቸው ተብለው ጥቅምት 5፣ 2008 ከእስር ተለቀዋል።

የዞን ዘጠኝ ጦማሪ የሆነው በፍቃዱ ኃይሉም የቀረበበት ክስ ከፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ጋር የማይገናኝ በመሆኑ በመደበኛው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 257/ሀ መሰረት በጽሁፍ አመጽ የመቀስቀስ መተላለፍን ፈጽሟል፤ ይሄንም ይከላከል ተብሎ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በጥቅምት 10፣ 2008 በተሰጠው ውሳኔ መሰረት በሃያ ሺህ ብር ዋስትና ከእስር መለቀቁ ይታወቃል።

ምንጭ፦ ዞን፱

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ