መንግሥት በሒልተን ሆቴል ላይ ያለውን ድርሻ ለመሸጥ እየተዘጋጀ ነው

የአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል
ኢዛ (ቅዳሜ መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 5, 2019):- ዘመናዊ የሆቴል አገልግሎት ባልተስፋፋበት ወቅት በኢትዮጵያ ቀዳሚ ባለኮከብ ሆቴል በመሆን የሚታወቀው የአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል 70 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ሊሸጥ ነው።
የአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል 70 በመቶው የመንግሥት ሲሆን፣ 30 በመቶው ደግሞ የሒልተን ኢንተርናሽናል ነው። አሁን ይሸጣል የተባለው የኢትዮጵያ መንግሥት 70 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ነው።
የመንግሥት የልማት ድርጅቶችና ይዞታ አስተዳደር ኤጀንሲ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ፤ የሒልተን ሆቴልን 70 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ በአሁኑ ወቅት የሆቴሉ አጠቃላይ ሀብት መጠን ምን ያህል እንደሆነ እየተጠና መሆኑን ገልጧል።
ጥናቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ጨረታ ወጥቶ አሸናፊ ለሚሆነው ይተላለፋል ተብሏል። (ኢዛ)