Artist Elias Melka

የአርቲስት ኤልያስ መልካን ነፍስ ፈጣሪ ን በገነት ያኑራት! - አሜን!!

ኢዛ (ሰኞ መስከረም ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 7, 2019):- በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የነበረው የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲና ጊታሪስት የሆነው ኤልያስ መልካ ሥርዓተ ቀብር ሰኞ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም. ተፈጸመ።

አርቲስት ኤልያስ በተወለደ በአርባ ሁለት ዓመቱ ባለፈው ቅዳሜ መስከረም 24 ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ሲሆን፣ የስኳር፣ የኩላሊትና የልብ ሕመም ገጥሞት ሕክምናውን ሲከታተል መቆየቱ ታውቋል።

ሰኞ መስከረም 26 ቀን 2012 በኢትዮጵያ በብሔራዊ ቴአትር ቤት በተዘጋጀ ፕሮግራም ሽኝት ተደርጎለታል። ከዚያም በመቀጠል በዕለቱ ከቀኑ በ9 ሰዓት ቤተሰቦቹ ወዳጆቹ ፣ የሥራ አጋሮቹ እና የጥበብ ባለሙያዎች፣ የሙዚቃ አፍቃሪያን በተገኙበት ሥርዓተ ቀብሩ በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኝ መካነ ቀብር ተፈጽሟል። (ኢዛ)

ከአዘጋጁ፣

የኢትዮጵያ ዛሬ ዝግጅት ክፍል በኢትዮጵያ ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ መልካም አሻራውን ባሳረፈው አርቲስት ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻል። ለቤተሰቡ፣ ለወዳጆቹና ለመላው አድናቂዎቹ መፅናናትን እንመኛለን። ፈጣሪ ነፍሱን በገነት ያኑራት! - አሜን!!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ