Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed wins the 2019 Nobel Peace Prize

የ2019 የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

ኢዛ (ዓርብ መስከረም ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 11, 2019):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 (እ.ኤ.አ.) የዓለም ሰላም ኖቤል ሽልማት ዛሬ አሸነፉ። በዓለም ሰላም ለማሸነፍ እንዲበቁ ያደረጋቸው ከ20 ዓመታት በላይ ከኤርትራ ጋር የነበረውን ፍጥጫ በሰላምና በስምምነት እንዲቋጭ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ መሆኑ ታውቋል።

በዓለም ላይ የሚገኙ መሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የእንኳን ደስ ያልዎት መግለጫ በማኅበራዊ ድረገጾች እያስተላለፉ ይገኛሉ።

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ዛሬ ዝግጅት ክፍልም ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ድስ ያላቸሁ ይላል። የአገሪቱ መሪዎች በዓለም ይታወቁበት የነበረውን መጥፎ ገጽታ፤ በበጎ መቀየር በመቻሉ ሁላችንም እንኳን ደስ ያለን! (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ