Sniper accessories caught at bole airport (November 05, 2019)

በሕገወጥ መንገድ በቦሌ ኤርፖርት በኩል ሊገቡ ሲሉ የተያዙ የስናይፐር አክሰሰሪዎች (የገቢዎች ሚኒስቴር ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ ያደረገው)

በዐረቢያ መጅሊስ ውስጥ ደብቆ ሊያስገባ የነበረው ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውሏል

ኢዛ (ማክሰኞ ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 5, 2019)፦ ሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር እየተስፋፋ መኾኑንና በተደጋጋሚ በፀጥታ ኃይሎች መያዙ ሲነገር የቆየ ቢሆንም፤ ዛሬ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዘ የተባለው የጦር መሣሪያ ግን አጀብ የሚያሰኝ ኾኖ ተግኝቷል።

የተያዙት የስናይፐር አክሰሰሪዎች

የገቢዎች ሚኒስቴር ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ እንዳደረገው፤ የተለያዩ የስናይፐር (ከርቀት አልሞ መተኮስ የሚችል ጠብመንዣ) አክሰሰሪዎች (መለዋወጫዎች) በቦሌ ኤርፖርት በኩል ሊገቡ ሲሉ ተይዘዋል።

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ስለጉዳዩ ይፋ ባደረገው መረጃ፤ በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ የግል መገልገያ ዕቃዎችን ሽፋን በማድረግ በዐረቢያን መጅሊስ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ተደብቆ ሊገባ ሲል መያዙን ጠቁሟል።

እነዚህን የስናይፐር የጦር መሣሪያ አክሰሰሪዎች በግለሰብ ስም ተደብቀው ሊገቡ የነበረ እንደኾኑም ተገልጿል። የስናይፐሮቹ አክሰሰሪዎች ሊያዙ የቻሉት በኤክስሬይና በዕቃ ፍተሻ ኦፊሰሮች መኾኑም ታውቋል። የስናይፐር አክሰሰሪዎቹን ይዞ ሊገባ ነበር የተባለው ተጥርጣሪ ግለሰብም በቁጥጥር ሥር መዋሉን መረጃው ያሳያል።

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ማኅበረሰቡ ሰላም ሊያደርፈርሱ የሚሠሩ ሕገወጥ ተግባራትን በመከላከሉ ሒደት ሁሉም የሕበረተሰቡ ክፍል የበኩሉን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል።

የዛሬውን ክስተት አስገራሚ ያደረገው፤ እንዲህ ያለ የጦር መሣሪያ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል በድፍረት ለማስገባት መሞከሩ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ