ሲኖዶሱ በሁሉም ቋንቋዎች ማሠልጠኛ ለመክፈት ወሰነ
ለትምህርት ቤቶቹ ቋሚ በጀት ይመደባል ተብሏል
ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 4, 2019)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሁሉም የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች ማሠልጠኛ እንዲከፈት ውሳኔ አሳለፈ።
የቤተክርስቲያኒቱን ተከታዮች በቋንቋቸው ማስተማርና ማገልገል እንዲቻል በሁሉም የአፍ ቋንቋዎች ማሠልጠኛ ማዕከል እንዲከፈት ሲኖዶሱ ውሳኔ ላይ ስለመድረሱ የገለጸው ዛሬ የተጠናቀቀውን ጉባዔ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።
ልዩ ልዩ ቋንቋዎች ተናጋሪ ክርስቲያኖችን በቋንቋቸው ለማስተማር እንዲቻል በየአገረ ስብከቱ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማጠናከር እንደሚገባ አስታውቋል። ከልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች አገልጋዮችን ለማፍራት እንዲቻል ለትምህርት ቤቶቹ ቋሚ በጀት ይመደባል ተብሏል። (ኢዛ)