ኮሮና ቫይረስ

ኮሮና ቫይረስን በምስል ለማሳየት በበሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል የተሠራጨ

በቫይረሱ የተያዙት ቁጥር 35 ደረሰ

ኢዛ (ዓርብ መጋቢት ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 3, 2020)፦ ዛሬ መጋቢት 25 ቀን ጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው ከኾነ፤ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 74 ሰዎች ውስጥ ስድስቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙትን ቁጥር 35 አድርሶታል።

ከነዚህ ስድስት ግለሰቦች ውስጥ አንዷ የድሬዳዋ ነዋሪ ስትኾን አምስቱ በአዲስ አበባ መኾናቸውን ከጤና ሚኒስቴር የወጣው መረጃ ያመለክታል። ይህች የድሬዳዋ ነዋሪ የኾነችው ግለሰብ የ33 ዓመት ዕድሜ ያላት ሲሆን፣ ከዚህ በፊት በኮሮና ቫይረስ መያዙ ከተገለጸ ግለሰብ ጋር ንክኪ እንደነበራት ታውቋል።

በአዲስ አበባ የተያዙት አምስቱም ወንዶች ሲሆኑ፤ የመጀመሪያው የ35 ዓመት ወንድ ሲሆን፣ ከዱባይ መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደመጣ ታውቋል። ሁለተኛው ደግሞ የ30 ዓመት ወጣት ሲሆን፣ እሱም መጋቢት 8 ቀን ከዱባይ መመለሱ ተረጋግጧል።

ቀሪዎቹ ሦስቱ የ28፣ የ56 እና የ30 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሲሆኑ፤ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው መኾኑ ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ