የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር

የ60 ዓመት ሴት ናቸው ያረፉት

ኢዛ (እሁድ መጋቢት ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 5, 2020)፦ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ አዲስ ተጨማሪ በቫይረሱ የተጠቁ አምስት ሰዎች መገኘታቸውን ካስታወቀ በኋላ፤ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ይፋ ባደረገው መግለጫ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ የ60 ዓመት ታማሚ ሕይወታቸው አልፏል።

ታማሚዋ መጋቢት 19 ቀን 2012 ዓ.ም. የቫይረሱ ምልክት ታይቶባቸው ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ.ም ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ሪፖርት ተደርጎ ነበር።

ባላፉት ስድስት ቀናት በጽኑ ሕክምን ላይ የነበሩት እኚህ ታማሚ ዛሬ እሁድ መጋቢት 27 ቀን ሕይወታቸው አልፏል። ዛሬ ከሰዓት በፊት የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አምስት በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች መገኘታቸውንና፤ ይህም በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች 43 መድረሱን መግለጹ ይታወሳል።

ከአምስቱ መካከል ሦስቱ ኢትዮጵያውያን፣ አንዱ ሊቢያዊና አንዱ ኤርትራዊ መኾናቸው ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ