በጽኑ ሕመም ላይ የነበሩት ወይዘሮ አረፉ
የጤና ሚኒስቴር
በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ሦስት ደርሰዋል
ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 10, 2020)፦ የዱከም ከተማ ነዋሪ የነበሩትና በቅርቡ የኮሮና ቫይረስ እንደተኘባቸው ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በጽኑ ሕክምና ላይ የነበሩት ታማሚ፤ ዛሬ ዓርብ ሚያዝያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።
የ65 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ሴት በሌላ ሕመም ሆስፒታል ገብተው የኮሮና ቫይረስ ምልክት ስለታየባቸው በተደርገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጦ፤ በጽኑ ሕክምና ክፍል ሕክምና ሲደረግላቸው የቆዩ ናቸው። ይህም በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የሞቱትን ሰዎች ቁጥር ሦስት አድርሶታል።
ዛሬ ከሰዓት በፊት የጤና ሚኒስቴር ዘጠኝ አዳዲስ ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰዎች ሪፖርት ማድረጉ የቫይረሱ ተጠቂዎች 65 መድረሱን ማሳወቁ አይዘነጋም። (ኢዛ)



