Total coronavirus cases in Ethiopia, 2020-04-17

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ (ዓርብ ሚያዝያ 9 ቀን 2012 ዓ.ም.፤ በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ)

ከአራቱ አዳዲስ በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ አንዱ ከዱባይ የመጣ ነው

ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 17, 2020)፦ ባለፉት 24 ሰዓታት 842 ሰዎችን በመመርመር አራት አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸውን በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰዎች ቁጥር 96 አድርሶታል። ከአራቱ አዳዲስ በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ አንዱ ከዱባይ የመጣ ነው።

ዛሬ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት አዲስ የቫይረሱ የተገኘባቸው አራት ሰዎች መካከል ሁለቱ የአዲስ አበባ፣ አንድ የባሕር ዳርና አንድ የአዲስ ቅዳም ነዋሪዎች ናቸው።

ከአዲስ አበባ ነዋሪዎቹ የ22 ዓመት ዕድሜ ያለው ወንድ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ የነበረ ሲሆን፣ ሁለተኛዋ የ52 ዓመት ሴት ስትሆን፤ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ ያልነበራት ነች። ሁለቱም በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ነበራቸው።

የባሕር ዳሩ ነዋሪ የ52 ዓመት ዕድሜ ያለው ወንድ ሲሆን፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለውና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ነው። አራተኛዋ ታማሚ የ23 ዓመት ዕድሜ ያላት የአዲስ ቅዳም ነዋሪ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላት ስትኾን፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንደነበራት እየተጣራ መኾኑን የዛሬው ሪፖርት የጠቁማል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ