Ministry of Health, Ethiopia

ጤና ሚኒስቴር

የተያዙት ቁጥር 114 ደረሰ

ኢዛ (ማክሰኞ ሚያዝያ ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 21, 2020)፦ አንድ ቻይናዊን ጨምሮ ሦስት በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በመገኘታቸው፤ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 114 ደረሰ።

ባለፉት ቀናት በሦስት ተከታታይ ሪፖርቶች በየአንዳንዱ ሪፖርት ሦስት፣ ሦስት አዳዲስ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ተገኝተዋል።

በዛሬው (ሚያዝያ 13 ቀን) የጤና ሚኒስትር ሪፖርት በ24 ሰዓታት 745 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጐ፤ ሦስት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል። ሁለቱ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሲሆኑ፤ አንዱ ደግሞ የ42 ዓመት ቻይናዊ ነው። ነዋሪነቱ ሰበታ ዞን የኾነው ይህ ቻይናዊ፤ የውጭ ጉዞ ታሪክ የሌለው በመኾኑ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ይኑረው አይኑረው እየተጣራ ነው።

ትናንት ሪፖርት በተደረገው የጤና ሚኒስትር መግለጫ ሦስት የቫይረሱ ተጠቂዎች የተገኙት ከድሬዳዋ ነው። በድሬዳዋ የተገኙት ሦስቱ ተጠንቀዎች የ11፣ የ15 እና የ18 ዓመት ታዳጊዎች ሲሆኑ፤ ሁለቱ ከጅቡቲ ወደ ድሬዳዋ ገብተው በለይቶ ማቆያ የነበሩ ናቸው።

ይህም ድሬዳዋን ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ከፍተኛ ተጠቂዎች የተገኙባት ከተማ አድርጓታል። የሰበታ ነዋሪ ቻይናዊን ጨምሮ በቫይረሱ የተያዙ ሦስት ሰዎች ተገኙ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ