አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሣ

በምዝበራ ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸውና ጥፋተኛ የተባሉት አቶ ታደሰ ካሣ (ግራ) እና አቶ በረከት ስምኦን (ቀኝ)

የቅጣት አስተያየት ይዘው እንዲቀርቡ ከነገ ወዲያ ተቀጥረዋል

ኢዛ (ሰኞ ሚያዝያ ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 4, 2020)፦ የጥረት ኮርፖሬትን ጥቅም በሚጎዳ መንገድ ተንቀሳቅሰዋል በሚልና ከዚሁ ጋር በተያያዙ አራት ክሶች ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የቆዩት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሣ በተከሰሱበት ክስ ጥፋተኛ ተባሉ።

ሁለቱ ተከሳሾች ሥራን በማያመች መንገድ መምራት፣ የሙስና ወንጀል በክልሉ ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመስርቶባቸው፤ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ሲመለከትና ክርክሩን ሲያደምጥ ቆይቶ፤ ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፤ አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።

ከእነአቶ በረከት ጋር ተከስሰው የነበሩት አቶ ዳንኤል ግዛው ደግሞ፤ ከቀረበባቸው የወንጀል ክስ ነፃ መባላቸው ታውቋል።

እነአቶ በረከት በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ አለመኾናቸውን በመግለጽ ሲከራከሩ የነበረ ቢሆንም፤ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ የጥፋተኛነት ውሳኔውን በማስተላለፉ፤ ተከሳሾቹ እና ዓቃቤ ሕግ የቅጣት አስተያየት እንዲያቀርቡ ከነገ በስቲያ ቀጠሮ መሰጠቱን የክልሉ ዓቃቤ ሕግ ገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ