መቀሌ

ትግራይ ክልል፣ መቀሌ

የትግራይ መገናኛ ብዙኀን እስካሁን ስለጉዳዩ አልዘገቡም

ኢዛ (ሰኞ ግንቦት ፲ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 18, 2020)፦ በትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌዎችን ለማስከበር በሚል በተፈጠረ ግጭት በመቀሌ አንድ ሰው ሲሞት፤ ሁለት መቁሰላቸው ተረጋገጠ።

በትናንትናው ዕለት (እሁድ ግንቦት 9 ቀን 2012 ዓ.ም.) ተፈጸመ የተባለው ግድያ፤ የተፈጸመው በጸጥታ ኃይሎች ነው። ፖሊስ በአንድ አካባቢ የተሰበሰቡ ወጣቶችን ለመበተን ባደረገው ጥረት በተፈጠረ ግጭት ግድያው ስለመፈጸሙ ተጠቅሷል።

በጸጥታ ኃይሎች በጥይት ከተገደለው አንድ ወጣት ሌላ ሁለት ወጣቶች በተመሳሳይ ተመትተው በመቁሰላቸው፤ በአሁኑ ወቅት በሕክምና ላይ ናቸው ተብሏል።

ከትናንቱ ግድያ ቀደም ብሎ በትግራይ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማስከበር በሚል አንድ ወጣት መጋቢት 19 ቀን 2012 ዓ.ም. በጸጥታ ኃይሎች መገደሉን መዘገባችን አይዘነጋም። የትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያወጀው የፌዴራሉ መንግሥት ከማወጁ ቀደም ብሎ መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ሲሆን፤ ከትናንቱ ግድያ ጋር በክልሉ በጸጥታ ኃይሎች የተገደሉትን ሰዎች ቁጥር ሁለት አድርሶታል።

ይህንን ግድያ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት እና በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰቦች እየተቃወሙት ይገኛሉ። የትግራይ ክልል መገናኛ ብዙኀን ግን በዚህ ግድያ ዙሪያ እስካሁን ምንም ዐይነት መረጃ አለማሰራጨታቸው፤ ነገሩን አስገራሚ አድርጎታል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ