በምዕራብ ወለጋ እየተወሰደ ባለ እርምጃ

ጃል መሮ፣ የኦነግ ሸኔ መሪ
36 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተገደሉ
169ኙ ደግሞ ተማርከዋል
ኢዛ (ሰኞ ኅዳር ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 16, 2020)፦ በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በወሰደው እርምጃ 36 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ሲገደሉ፤ 169ኙ ታጣቂዎችን መማረካቸው ተገለጸ።
የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በዚህ ጉዳይ ላይ ያሰፈረው መረጃ፤ “በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በወሰደው ሕግን የማስከበር እርምጃ፤ የጁንታው ተላላኪ ሸኔ ታጣቂዎች ሲደመሰሱ፤ 169 ተማርኳል። ለጁንታው ተላላኪዎች ድጋፍ በመስጠት የተጠረጠሩ 96 ሰዎችም ተይዘው ጉዳያቸው እየተመረመረ ነው” ብሏል። (ኢዛ)