በኑሩንበርግ ከተማ (ጀርመን) የተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ
በጀርመኗ የኑሩንበርግ ከተማ ፌብሩዋሪ 17 እና 18 ቀን 2012 ዓ.ም. የከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች ህዝባዊ ስብሰባ አካሂደዋል። ፌብሩዋሪ 17 ቀን ከሂዩማን ራይት ዎች ጋር በትብብር በተዘጋጀው ውይይት ላይ የሕግ ባለሙያዎች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተወካዮች ተገኝተዋል።
በማግስቱ ፌብሩዋሪ 18 ቀን ደግሞ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳሩ መጥበብ ያሳሰበው የፖለቲካና ሲቪክ ማኅበራት ድርጅት በኑሩንበርግ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ የምክክር መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የፖለቲካ መሪዎች፣ የኃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ የመገናኛ ብዙኀን ሙያተኞች፣ የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያውን ተካፍለዋል። የሁለቱን ቀን ውይይት አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰውን ዘገባ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!