‘የተቃወመው የአፋር ህዝብ አይደለም’ ኢንጂኒየር ኃይሉ ሻውል

Ethiopia Zare (ዓርብ ነሐሴ 7 ቀን 2001 ዓ.ም. August 14, 2009)፦ መኢኣድ ባለፈው እሁድ በዳግማዊ ምኒልክ ባደረገው ህዝባዊ ስብሰባ የተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀውን የሠንደቅ ዓላማ ዓርማ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ የተቃወመ ሲሆን፣ የአፋር ክልላዊ መንግሥት ዓርማውን መቃወም የብሔረሰቦችን መብት መቃወም ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል።

 

ክልላዊ መንግሥቱ ባወጣው ጠንካራ መግለጫ “መኢአድ የብሔር ብሔረሰቦችን መብት የማይቀበል ሕገ መንግሥቱንም የዜጎችን እኩልነትም የማይቀበል ነው” ብሎታል።

 

ኢህአዲግ በስልታዊ አካሄድ መኢአድ ላይ አፋርን ልኮበታል ያሉ ታዛቢዎች፤ “ገና የሌሎች ክልል መንግሥታትም ተራ በተራ መኢአድን በመቃወም መግለጫ ያወጣሉ” ብለዋል።

 

የመኢአድ ፕሬዝዳንት ኢንጂንየር ኃይሉ ሻውል “የተቃወመው የአፋር መንግሥት እንጂ የአፋር ህዝብ አይደለም፤ ለኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ በመቆርቆር የአፋር ህዝብ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የአፋር ኃይማኖታዊ መሪ ቢትወደድ ኣሊሚራህ “የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ እንኳን እኛ ግመሎቻችን ያውቁታል” በማለት መግለፃቸው የሚታወስ ነው” ብለዋል።

 

የክልላዊ መንግሥቱን ተቃውሞ ያጣጣሉት ኢንጂንየር ኃይሉ “ኢህአዲግ በዓለም ህዝብ ውሣኔ ከሚጠየቅባቸው ጉዳዮች አንዱ ሠንደቅ ዓላማ ነው። ገዢው ፓርቲ በሚቆጣጠረው ምክር ቤት በሕግ አስወስኖ ህዝቡን ይህን ካላደረግህ በማለት ሊያስገድደው አይገባም ብለዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ