Ethiopia Zare (ሐሙስ ነሐሴ 14 ቀን 2001 ዓ.ም. August 20, 2009)፦ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተመረቀውና “የሚሊኒየሙ ድልድይ” ወደ ተባለው የዓባይ ወንዝ መሸጋገሪያ የሚወስደው “ዘመናዊ” መንገድ ጎሃ ጽዮን ላይ በመደርመሱ መንገድ ተዘግቶ ግንኙነት ተቋርጦ እንደነበር ተዘገበ።

 

ነሐሴ 13 ቀን 2001 ዓ.ም. ከጎጃም ወደ አዲስ አበባና ከአዲስ አበባም ወደ ጎጃም የሚያመሩ ከባድ መኪናዎች ጉዞአቸው ተስተጓጉሏል።

 

በጎሃ ጽዮን ክልል ወደ ዓባይ ወንዝ እና ወደ “ሚሊኒየሙ” ድልድይ መቃረቢያ ላይ ያጋጠመው የመሬት መንሸራተት የተለመደ ነገር ነው” በማለት መልስ የሰጡት የሀገሪቱ የአውራ ጐዳና መ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፤ “መንገዱ በዘመናዊ ሁኔታ ሲሠራ በጥናት አልነበረም ወይ?” ለሚለው ጥያቄ አርኪ መልስ መስጠት አልቻሉም። ጎሃ ጽዮን ላይ ረቡዕ ዕለት መሬቱ ሲንሸራተት “ዘመናዊ የተባለለትን” አስፋልት በብዙ ሜትር ርቀት ደርምሶ ከጥቅም ውጪ አድርጎት የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት መንገዱ መጠነኛ ጥገና ተደርጎለት ሥራ መጀመሩን ለማወቅ ችለናል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ