Ethiopia Zare (ዓርብ ነሐሴ 22 ቀን 2001 ዓ.ም. August 28, 2009)፦ ኢ.ካ.ዜ.ሊ. በመባል የሚታወቀውና መቀመጫውን ካልጋሪ - ካናዳ ያደረገው ኢትዮጵያዊ ካናዳዊያንን አሰባስቦ የሚንቀሳቀሰው ሊግ በኢትዮጵያና በአፍሪካ የሰፈነውን አምባገነንነትንና ዘር ማጥፋትን ለማስቆም በእ.ኤ.አ. መስከረም 13 ቀን ለሚደረገው ሰልፍ ድጋፍ በመስጠት መግለጫ አወጣ።

 

በካናዳ በአምስቱም ቅርንጫፎቹ ማለትም በቫንኩቨር፣ ካልጋሪ፣ ኤድመንተን፣ ዊኒፔግና ኦታዋ የሚገኙትን አባላቱንና ደጋፊዎቹን ለሰልፉና ለሰልፉ ተልዕኮ መሳካት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ እንዲሁም ማንም በቅርብ ርቀት የሚገኝ ሠላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሰልፉ እንዲገኝ ጥሪውን አቀርቧል።

 

ይሄው የምርጫ 2005ን አፈናና ወከባ ተከትሎ በካናዳ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን አቋም ለማንጸባረቅና እንቅስቃሴያቸውንም ለማስተባበር በዚያኑ ዓመት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ካናዳዊያን ዜጎች ሊግ (ኢ.ካ.ዜ.ሊ) በእንግሊዘኛው ምህጻረ ቃል ECCL እየተባለ የሚጠራው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ኦገስት 25 ቀን ባወጣው መግለጫ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የአሜሪካን ሕግ ማውጫና መወሰኛ ምክር ቤት ህንጻ ፊት ለፊት የሚደረገውን አምባገነንነትንና ዘር ማጥፋትን የሚያወግዘውንና ባስቸኳይ እንዲቆምም ለአሜሪካ መንግሥት ጥሪ የሚያቀርበውን ይሄንን ሰልፍ ደግፎ ባወጣው መግለጫ ዘር ማጥፋትን ማቆም የሕግ የበላይነትን ማስፈንና ዲሞክራሲንና ፍትህን በኢትዮጵያ ለማስፈን የሚደረገው ትግል የማንም ሳይሆን የኢትዮጵያዊያን ሁሉ መሆኑን ጠቁሟል።

 

በዚህ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር እሁድ መስከረም 13 ቀን በሚደረገው ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንዲገኙና ትብብራቸውን እንዲያሳዩ ጠይቋል።

 

ምዕራባዊያን ሀገሮች በኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን ፖሊሲ እንዲቀይሩና አምባገነንነትንና ዘር ማጥፋትን የሚፈጽም ሥርዓትን በማገዝ ፋንታ ሀገሪቱ አዎንታዊ ወደ ሆነ አቅጣጫ የምትለወጥበትን አካሄድ እንዲቀርጹ ለማድረግ ስለሚረዳ፤ በዚህ ሰልፍ ላይ መገኘት አስፈላጊ መሆኑን መግለጫው ያትታል። የመግለጫው ሙሉ ቃል www.ethiocan.org ላይ ያገኙታል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ