Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነሐሴ 26 ቀን 2001 ዓ.ም. September 1, 2009)፦ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 2ኛ የወንጀል ችሎት፤ ከአንድ ዓመት በፊት በምሥራቅ ወለጋ በሚገኙ ሦስት የቤኒሻንጉል ጉምዝ “ክልል” አዋሳኝ ሥፍራዎች “የግድያ፣ የዝርፊያ፣ የአስገድዶ መድፈርና የንብረት ማውደም ወንጀል ፈጽመዋል” ባላቸው 101 ተከሳሾች ላይ የመጨረሻ የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ ለነሐሴ 27 ቀን 2001 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

 

አስቀድሞ በነበረው የክስ መመልከትና ብይን የመስጠት ሂደት ተከሳሾቹ “ወንጀለኞች እና ጥፋተኞች መሆናቸውን አረጋግጫለሁ” ያለው ፍ/ቤቱ፤ ተለዋጭ ቀጠሮውን በሰጠበት ዕለት ማለትም ነሐሴ 20 ቀን 2001 ዓ.ም፤ የዓቃቤ ሕጉን እና የተከሳሾቹን የመፋረጃ ሃሳብ አድምጧል።

 

በእነ ታደሰ ጀዋሬ የክስ መዝገብ ውስጥ የተካተቱ 101 የጉምዝ ብሔር ተወላጅ የሆኑት ተከሳሾች ሁሉም በወህኒ ቤት የሚገኙ ሲሆን፣ ከግንቦት 9 እስከ 13 ቀን 2000 ዓ.ም. ድረስ በነበሩት ቀናት ሳሲጋ በተባለው የወለጋ ወረዳ ውስጥ በከፈቱት የማጥፋት፣ የመዝረፍ፣ የመግደል እና አስገድዶ የመድፈር ዘመቻ፤ በአንገር ሸንኮራ፣ በ4ኛ ካምፕ እና በአንገር ሚቴ ሠፈሮች ውስጥ፤ ከ20 የሚልቁ ንፁሃን ዜጎችን ገድለዋል፣ በርካቶችን አቁስለው ለአካለ ስንኩልነት ዳርገዋል፣ ከ300 የሚበልጡ ቤቶችን አጋይተዋል፣ ባለቤቷን የገደሉባትን ሴት ለሰባት ሆነው ደፍረዋል፣ በርካታ ንብረቶችን ዘርፈዋል በሚል የተከሰሱ ናቸው።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ