Ethiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2002 ዓ.ም. September 24, 2009)፦ በምዕራብ ጐጃም የአንድነት ቅርንጫፍ ቢሮ አስተባባሪዎች ላይ መስከረም 11 ቀን 2002 ዓ.ም. ድብደባ ተፈጸመ። ወከባና ዛቻ የገጠማቸው የፓርቲው አስተባባሪዎች አንድነት ፓርቲን "ፀረ-ህዝብና ፀረ-ሠላም ነው" ብለው እንዲክዱት ከፍተኛ ጫና ተደርጎባቸዋል።

 

ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጽ/ቤት አዲስ አበባ የደረሰውን የስልክ ሪፖርት ዋቢ የጠቀሱት ምንጮቻችን እንዳብራሩት፤ የምዕራብ ጐጃሞቹ የብአዲን ካድሬዎችና ታጣቂዎች የአንድነት ፓርቲ ዋንኛ ደጋፊ የሆኑትን አንድ አዛውንት ወደ ቤተክርስቲያን ወስደው በምዕመናን ፊት ፓርቲውን የካዱና ከአንድነት ሰዎች ጋር የፈጠሩትን ግንኙነት ወንጀል እንደመሥራት ቆጥረው ቃል እንዲገቡለት ሊያስገድዷቸው ሞክረዋል።

 

ይሁን እንጂ መስከረም 12 ቀን 2002 ዓ.ም. በወርሃዊው የቅዱስ ሚካኤል የክብር ቀን በቤተክርስቲያን በግዳጅ እንዲገኙ የተደረጉት አዛውት "አንገቴን ቆርጣችሁ ትጥላላችሁ እንጂ ለሠላምና ለፍትህ መስፈን ትግል የሚያደርገውን ፓርቲዬን አልክድም" በማለታቸው የታጣቂዎቹ እና የካድሬዎቹ ፍላጐት ለጊዜው አልተሳካም።

 

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአርባምንጭ ለሁለተኛ ጊዜ ተከፍቶ የነበረው የአንድነት ቅርንጫፍ ቢሮ መዘጋቱንና ቤታቸውን ለፓርቲው ቢሮነት ያከራዩ ግለሰብም የታሰሩ መሆናቸውን ሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2001 ዓ.ም ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ጠቁሟል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ