ኢህአዲግ ወደ ድርጅት ሊቀየር ነው
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ኅዳር 1 ቀን 2002 ዓ.ም. November 10, 2009)፦ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር በሚል ስያሜ ይጠራ የነበረው ኢህአዲግ ከምርጫ 2002 በኋላ የቅርጽ ለውጥ እንደሚያደርግ ውስጥ አዋቂዎች ገለጹ።
ሕብረ ብሔራዊ አካሄዱን ለመክላት እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል ያሉት እነዚሁ ምንጮች፤ ትልቁን የማፍረስ ሥራ የሚያካሂደው ግንባርን አፍርሶ በፓርቲ ወይም በሕብረት ወይም ደግሞ በድርጅት ስም ሲለውጥ ትልቁን ሥራ ይሠራል ብለዋል።
ግንባሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዕድሜውን ለማርዘም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነው ያሉት ውስጥ አዋቂ ምንጮች፤ በተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ የሚሰነዘርበትን “ግንባር ሆኖ ሀገር መምራት አይችልም” የሚል ነቀፌታ ለማስቀረትም ይረደዋል ተብሏል።
የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ለመጠቀም አሁን ባለበት አደረጃጀት መቀጠል ስለማያስችለው ነው ግንባርን የሚያፈርሰው የተባለለት ይሄው ግንባሩን የመለወጥ ተግባር፤ በቅርቡ የዚሁ ተግባር አንዱ አካል የሆነውን የቤኒሻንጉል ህዝቦችን ከብሔር መካለል ወደ አንድነት እንዲመጡ ያደረገ ሲሆን፣ በዞኑ የሚገኙትን ሦስት ሕብረብሔር ድርጅቶችን በአንድ ጨፍልቆ የሺናሻ ህዝቦች መሪ የሦስቱ ድርጅቶች መሪ ሆኗል።
በብሔር ተከልለው የነበሩ ድርጅቶች ተጨፍልቀው የደቡብ ህዝቦች፣ የአማራ ህዝቦች የኦሮሚያ ህዝቦች ሊባል እንደሚችልም ያላቸውን መረጃ ምንጮቹ ጠቁመዋል።



