1430ኛው የአረፋ በዓል ነገ ይከበራል
Ethiopia Zare (ኀሙስ ኅዳር 17 ቀን 2002 ዓ.ም. November 26, 2009)፦ አንድ ሺህ አራት መቶ ሠላሳኛው የአረፋ (ኢድ አል-አድሃ) በዓል በመላው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዘንድ ነገ አርብ ኅዳር 18 ቀን 2002 ዓ.ም. ተከብሮ ይውላል።
በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዘንድ በታላቅ ድምቀት ከሚከበሩት የእስልምና ኃይማኖት በዓላት ውስጥ አንዱ የሆነው የአረፋ በዓል መሆኑ ይታወቃል።
የአረፋ (የኢድ አል-አድሃ) በዓል ነብዩ ኢብራሂም ልጃቸው ኢስማኤልን እንዲሰዋ ፈጣሪ ያዘዘውን ትዕዛዝ ሊፈጽም ሲል፤ በምትኩ በግ ማረዱን ለማስታወስ የሚከበር በዓል ነው።
በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የአረፋ በዓል የሆንላችሁ ዘንድ ትመኛለች።



