Ethiopia Zare (ሐሙስ ኅዳር 24 ቀን 2002 ዓ.ም. December 3, 2009)፦ ኢትዮጵያውያን የሐጅን ሥራ ለመፈጸም ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ሔደው የነበሩ ሐጃጆች በአውሮፕላን እጦት ምክንያት ወደ ሀገራችን መግባት እንዳልቻሉ ከአዲስ አበባ ምንጮች አረጋገጡ።

ከሳዑዲ ዐረቢያ ስልክ ደውለው ለዜና ማሠራጫዎች ይነገርልን ያሉት እነዚህ ሐጃጆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅድሚያ ለሌሎች ሀገራት ዜጎች በመስጠቱ እኛን ለተጨማሪ ወጪ እየዳረገን ነው ብለዋል።
ለአየር መንገዱ ከኢትዮጵያ ሳንወጣ ሙሉ ክፍያ ከፍለው የነበረ ቢሆንም በሚፈለገው ጊዜ መስተናገድና ወደ ሀገራቸው መመለስ ባለመቻላቸው ሐጃጆች የሐጅ ሥራው ከተፈጸመ በኋላ ያለምንም ሥራ በሆቴልና በምግብ ወጭ ገንዘባቸውን በመጨረስ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተጭሏል።
 
አየር መንገዱ ለናይጄሪያ ሐጃጆች ቅድሚያ የሰጠው ከክፍያ አንጻር ቢሆንም 5 ሺህ የሚሆኑ ሀጃጆችኑ ኢትዮጵያዊያ ሀገራቸው ለመመለስና መደበኛ ስራቸውን ለመቀጠል አለመቻላቸውና ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰአት ማንም አ ነት ምላሽ አለማግኘታቸው ተገልጿል።

ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ብናደርግም በትክክል ምላሽ ሊሰጠን የሚችል ሰው አላገኘንም።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ