አምስት ሕፃናትና ስምንት ሴቶች ይገኙበታል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ኅዳር 29 ቀን 2002 ዓ.ም. December 8, 2009)፦ አስዋን ከተማ በሚገኘው ችላል ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ 17 ኢትዮጵያዊያን ሁለት ወላጅ አልባ ሕፃናቶችን ጨምሮ ለሁለት ዓመታት በእስር ላይ እየተሰቃዩ መሆኑን ገለጹ።

 

ወታደራዊ ካምፑ ከከተማ ወጣ ያለና ምንም አይነት የውጭ ድርጅቶችም ሆኑ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የማይጎበኙትና የስቃይ ካምፕ መሆኑን ከቦታው ወደ ካናዳ የገቡ ሰዎች የዓይን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

 

ስደተኞቹ ሱዳን ከሁለት እስከ 20 ዓመታት የቆዩ ሲሆን፣ ወደ ግብጽ ከገቡ ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ በወታደራዊ ካምፑ ውስጥ መጠነኛና ለሁለት ዓመታት ተመሳሳይ ምግብ እየተመገቡ መኖራቸውን ገልጸዋል። እነዚሁ በስቃይ ላይ ከሚገኙ 17 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ውስጥ ሁለት ወላጅ አልባ ሕፃናቶችን ጨምሮ አምስት ሕፃናት እና ስምንት ሴቶች ከመሆናቸውም በላይ ወጣቶችና ጎልማሶችም እንደሚገኙበት ለመረዳት ችለናል። በተለይ ራስን በሚያስችሉ ሀገሮች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካሉበት ስቃይ እንዲወጡም እንዲታደጓቸው ጠይቀዋል።

 

የተባበሩት መንግሥታት ከካምፑ ቅጥር ግቢ ውጭ አስጠርቶ አነጋግሮ ምንም አይነት እርዳታ ላደርግ አልችልም እንዳላቸውና ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ በማይችሉበት ሁኔታ ያለምንም ፍርድ ቤት ክስ በካምፑ ውስጥ ለስቃይ መዳረጋቸውን እስረኞቹ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገልጸዋል።

 

በተመሳሳይ በካምፑ ውስጥ ታስረው የነበሩ የኤርትራ ሰዎች ግን በካናዳ መንግሥት ትብብር ወደ ካናዳ እንደገቡ ታውቋል።

 

ወገኖች ይህንን ችግራቸውንን ተረድተው ለዓለም መንግሥታትና ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ድምጻቸውን እንዲያሰሙላቸውም ተማጽነዋል።

 

እስረኞቹ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይ ከጎንደር፣ ከጅማ፣ ከትግራይ፣ ከወላይታና አዲስ አበባ ወደ ሱዳን፤ ከዛም ወደ ግብጽ የገቡ ስደተኞች ሲሆኑ፣ ከስፍራው የደረሰን ስም ዝርዝራቸውን እንደሚከተለው ይነበባል።

 

  1. ብርሌ ማሞ ፋንታ፣ ዕድሜ 18
  2. አብረሀም ግደይ ገ/ማሪያም፣ ዕድሜ 47
  3. ተክላይ ገብሬ ተክሌ፣ ዕድሜ 42
  4. ሰረት ተክላይ ገብሬ፣ ዕድሜ 10
  5. ተመስገን ተክላይ ገብሬ፣ ዕድሜ 4
  6. ኤርሚያስ ተክላይ ገብሬ፣ ዕድሜ 7
  7. አብዱቃድር ናስር ኢብራሂም፣ ዕድሜ 26
  8. እንዳልካቸው ወልዴ ደሴ፣ ዕድሜ 23
  9. ተስፋይ ህለሳ ገ/ዋህድ፣ ዕድሜ 30
  10. ዘውዴ ተወልደ ወርቅነህ፣ ዕድሜ 35
  11. ሙሉ ወርቁ አድማሴ፣ ዕድሜ 25
  12. ረቅያ ሁሴን ማሀመድ፣ ዕድሜ 16
  13. ሙሉ አንተነህ ወርቅነህ፣ ዕድሜ 24
  14. ማርታ ማሞ ረዳ፣ ዕድሜ 29
  15. ትእግስት ዮሀን መሌሩ፣ ዕድሜ 29
  16. ደሞዝ ገብሬ ደስታ፣ ዕድሜ 36
  17. ተስፋዮ እያሱ ወ/ሚካኤል፣ ዕድሜ 35

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ