Ethiopia Zare (ሰኞ ታህሳስ 12 ቀን 2002 ዓ.ም. December 21, 2009) ፦ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕዝብ እንዳራሴ የሆኑት የፓርላማ አባላት ከስብሰባ የሚቀሩት ተመራጮች ቁጥር ማሻቀቡ ታወቀ።
 
     
ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ አቶ ግርማ ብሩ በስኳርና ነዳጅ ዋጋ ንረት ጋር በተያያዘ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሪፖርት ለማዳመጥ መገኘት ከሚገባቸው 547 መቀመጫ ያላቸው አባላት መካከል የተገኙት 317 ብቻ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱንና በአፈ ጉባኤው በተደጋጋሚ አቤቱታ እንደቀረበበት የገለጹልን የፓርላማ አባላት ከአቤቱታው በኋላ በስብሰባ የማይሳተፉ እንደራሴዎች ቁጥር መጨመሩን ገልጸዋል።

በፓርላማ የነዳጅን መጨመርና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው አቶ ግርማ ብሩ የነዳጅን ጭማሪ ምላሽ ሳይሰጡበት ያለፉ ሲሆን በምክንያትነት ያቀረቡት ጥያቄውን ያቀረቡት የፓርላማ አባል ባለመገኘታቸው ነው ብለዋል።

የስኳር ዋጋ የጨመረው በዓለም ትልቁ የስኳር አምራች በሆነቸው ሕንድ አገር በተፈጠረው የምርት እጥረት እንደሆነ የተናገሩት አቶ ግርማ ብሩ በዓለም ገበያ ዋጋው በመናሩንና ከውጭ ማስገባት አለመቻሉን ገልጸዋል። ሀገሪቱ ለውጭ ምንዛሪ ትልከው የነበረውን የስኳር ምርት በጠቅላላ አቁማ ለአገር ውስጥ ብቻ እንዲውል አድርጋለች ተብሏል።
ዋጋውን ያናሩት ተጫራቶች ናቸው ያሉት አቶ ግርማ በ15 ቀን 80 ሺህ ኩንታል ይቀርብ የነበረው ወደ 120 ሺህ እንዲያድግ ተደርጓል ብለዋል።

 
እለት ተዕለት እያደገ የመጣው የስኳር ዋጋ በኪሎ ከ15 እስከ 17ብር እየተሸጠ ሲሆን በየወሩ ዋጋ ማስተካከያ ይደረግ የነበረበት ነዳጅ ግን በዓለም ዋጋ ቅናሽ ቢያሳይም በችርቻሮ አለመቀነሱ አሳሰቢ ሆኗል።
 
የፓርላማ አባላት የሥራ ጊዜያቸው ለማብቃት ከ6 ወር ያላነሰ ጊዜ አላቸው።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ