Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 17 ቀን 2002 ዓ.ም. December 26, 2009)፦ “የፓርቲውን እንቅስቃሴ በተደጋጋሚ አውከዋል” የተባሉት የእነፕሮፌሠር መስፍንን ቡድን ለገርጂ ፖሊስ ጣቢያ ክስ መስርቶ የነበረው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ክስ ፖሊስ ማቋረጡ ተሰማ።

 

እንደምንጮቻችን ገለጻ ከሐምሌ ወር ጀምሮ ፓርቲውን ሲያውኩ የነበሩትን ሰዎች ክስ ፖሊስ መስማቱን ያቋረጠው “ክሱን የመመርመር ሥልጣኑ የኔ ሳይሆን የፍትህ ሚኒስቴር ነው” በማለቱ ነው። በኢንጂንየር ግዛቸው ሽፈራው የቀርበው ክስ ተከሳሾች ቀርበው ምስክር ተሰምቶ የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ክሱን አቋርጦታል።

 

ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ፓርቲው ሕጋዊ ሥርዓቱን የሚጠይቁ የሕግ አግባቦችን ተከትሎ ጉዳዩ በሕግ እንዲታይ ከማድረግ ወደኋላ እንደማይል ነው።

 

ይህ በእንዲህ እንዳለ በፕሮፌሠር መስፍን የሚመራው ቡድን “መርኅ ይከበር!” የሚለውን አቋሙን እንደገፋበት ሲሆን፤ ሰሞኑን በፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ አባላት የተደረገውን የሥልጣን ሽግሽግ በማወገዝ መግለጫ አውጥቷል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ