መድረክንና መኢአድን ያወዛገበው የአውራ ጣት ምልክት ለመኢአድ ተሰጠ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 1 ቀን 2002 ዓ.ም. January 9, 2010)፦ በአውራ ጣት የምርጫ ምልክት ውዝግብ ውስጥ በገቡት በመድረክ እና በመኢአድ መካከል ውሳኔ ያላገኘው መድረክ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ አውራ ጣትን በአምስት ጣት እንዲቀይር ተደረገ።

 

ዛሬ ከቀትር በኋላ መድረክ ለምርጫ ቦርድ ባቀረበው ማመልከቻ መሠረት የአምስት ጣት (የሠላምታ ምልክት) ዓርማ እንዲጸድቅለት የጠየቀ ሲሆን፤ ምርጫ ቦርድ እንደሚቀበለው እምነቱ መሆኑን አንድ የመድረኩ አመራር አባል ገልጸዋል።

 

መድረክ ለምርጫ ቦርድ በጻፈው ደብዳቤ “ቀደም ሲል የመረጥነው አውራ ጣት ምልክት ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ስላልፀደቀ ሌላ ምልክት እንድንመርጥ ታህሳስ 26 ቀን 2002 ዓ.ም. በቁጥር አ573/ፓአ/ተ/330 ሌላ ምልክት እንድንመርጥ ደብዳቤ የተፃፈልን መሆኑ ይታወሳል። በዚሁ መሠረት የእጅ ሠላምታ ምልክት (አምስት ጣቶች ያሉት) የመረጥን ስለሆነ በዚሁ መሠረት ይኸው ምልክት እንዲጸድቅልን በትህትና እንጠይቃለን።” በማለት ማመልከቻውን አስገብቷል።

 

ቀደም ሲል መድረክን እና መኢአድን ሲያወዛግብ የነበረው የአውራ ጣት ምልክት በኢንጂንየር ኃይሉ ሻውል ለሚመራው የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መሰጠቱን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገልጸዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ