“ኢሳት ሁለት ወር ቀደም ቢል ኖሮ ምርጫው የኛ ይሆን ነበር” አስተያየት ሰጪዎች

በተክለሚካኤል አበበ

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ የተከታታዮቹ ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን የአይን ምስክሮች ገለጹ። ከምርጫው በፊት ቢጀመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርግ እንደነበር ተገለጸ።

 

ወጣት ለይኩን ሙልጌታ ይሄንን “ምርጫ” ምርጫ አድርጎ ስለማይቀበለው፡ የመራጭ ካርድ አልወሰደም። ቢሆንም ግን ያገሩ ነገር ሁሌም ያብከነክነዋል። ስለዚህ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት እንደተጀመረ ሲሰማ፡ ከቤቱ የሰቀላትን ሳተላይት መጎርጎር ጀመረ።

 

መጀመሪያ ከውጭ በኢሜይል በደረሰው የጣቢያ ቁጥር ሲጎረጉር የየመን ሬድዮ ፕሮግራም ላይ ወሰደው። ከትንሽ ቀን እንግልት በኋላ ግን ባለጣቢያዎቹ “ኢሳት” እሱና ወዳጆቹ ደግሞ “እሳት” የሚለውን የቴሌቪዥን ጣቢያ ደረሰበት። የእንጊሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወይም የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ቤቱ ቢገባ ያን ያህል አያስደስተውም። ከቴሌቪዥን ጣቢያው መስራቾች መግለጫ ውስጥ ያልተካተቱ ሁለት ተጨማሪ መረጃዎች የጣቢያውን ፍለጋ እንዳጓተተበት ነግሮናል ይኸው ሰው። የኢሳት መግለጫ የጠቀሰው Arabsat / Badr 6/ Ku band፣ Channel Frequency: 11785 GHz፣ Symbol Rate: 27500 MSym/s፤ Polarization: Vertical፤ ሲሆን፡ ይኸው አስተያየት ሰጪ የጠቀሰው ጣቢያ ግን ከላይ ከተጠቀሱት ቁልፎች ባሻገር ArebSat 2A፡ FEC: ¾፡ Polarity: Vertical፡ VPID: 410 APID: 420፡ PCRPID 410 የተሰኙ መረጃዎችን ይዟል ብሏል።

 

እስከ ትናንት፡ አርብ፡ ግንቦት 13 (ሜይ 21) ከኢትዮጵያ ባገኘናቸው መረጃዎች መሰረት፡ ከአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጀምሮ፡ ተዘዋውሮ አስተያየት በጠየቀባቸው ቦታዎች ሁሉ፡ የሰዉ ጉጉትና ምላሽ እጅግ የሚያስደስት ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሰራተኛ የሆነ አንድ ወጣት ለጓደኛው በጻፈው ኢሜይል ላይ እንዲህ ብሏል። “ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ የኒቨርስቲ ሰራተኞች ክበብ ውስጥ ለቁርስ ስገባ የተከፈተው ቴሌቪዥን ኢሳት ነበር። ፕሮፌሰሮቹን ጨምሮ ብዙ ሰዎች እቴሌቪዥኑ ስክሪን ስር ተደቅነው ይመለከቱ ነበር። ለምን ያህል ግዜ እንደተደጋገመ አላውቅም፡ ባጋጣሚ የተከፈተው የአና ጎሜዝ ቃለምልልስ ነበር። በነገራችን ላይ ዛሬ ማታ የሚተላለፈው ፊልም “የውበት ስደት” ('The migration of beauty' ) የተሰኘው በምርጫ 2005 ቅሌት ላይ ተመርኩዞ የተሰራው ፊልም ነው። ካየሁት በኋላ አጋራሀለሁ። ኢሳትን በተመለከተ ግን፡ ካገኘነው ግዜ ጀምሮ በቤታችን መደበኛው ጣቢያ እሱ ሆኗል ብሏል። በወሳኝ ሰዓት ነው የመጣው። የወያኔ ሚዲያ የሚደብቀውን በማጋለጡ ረገድ ጥሩ አማራጭ ይሆናል።” ብሏል። (… Wow! I was in the AAU staff lounge for breakfast. The TV was ESAT and many people including the professors were watching zoom getting very close to the TV screen…… I will share you after watching. About the TV since we found it is the default in hour house and it has come at a very crucial time. A good option if it can disclose what the EPRDF media conceals…)

 

ሌላው የአዲስ አበባ አስተያየት ሰጪ፡ “ፕሮግራሙን እየኮሞኩምነው ነው፡ እስካሁን ከደርዘን ለሚበልጡ ሰዎች ነግሬያለሁ፡ ለሌሎች ወገኖቻችንም እናጋራቸዋለን ብሏል። “We are enjoying the program and will share it with fellow citizens. So far I have shared the information with dozens of people”። ሌላው አዋሳ የሚገኝ ምንጭ፡ “ትናንት የአና ጎሜዝ ቃለምልልስ በኢሳት ላይ ተላልፎ ሳይ ተደነቅኩኝ። እስካሁንም ድረስ ለኢትዮጵያ መልካም ስራ የምትሰራ ጠንካራ ሴት ነች። በኢትዮጵያዊያን እንደተሰየመችው፡ እውነትም “ሀና ጎበዜ”፡ ነች።” ብሏል። “Yesterday Anna Gomez's interview was aired on ESAT and I was astonished. She is still working very strong for the good of Ethiopians. Truly she is 'Hana Gobeze' as she was named by Ethiopians.”

 

ሌላዋ በጽሁፍ አስተያየት ልትሰጠን ያልፈቀደችውና፡ ኢሳት ትንሽ ቀደም ብሎ ቢመጣ፡ 2005 ይደገም ነበር ያለችው አስተያየት ሰጪ፡ “በሰላማዊ ትግል አምነው የሚታገሉ ሰዎችን ጥረት ብናደንቅም፡ አሁንም ቢሆን በዚህ ምርጫ ለውጥ ይመጣል ብሎ የሚጠብቅ የዋህ የለምና፡ “ልማታዊ ጋዜጠኝነት” እያለ ከሚያደነቁረን ቴሌቪዥን የሚገላግለን ቴሌቪዥን መምጣቱ ከምርጫውም ባሻገር ለሚኖረን ትግል ወሳኝ ነው።” ብላለች። ይህችው ወጣት ግን ጠላት የመረጃ ፍሰትን ለመቆጣጠር ካለው ጽኑ ፍላጎት የተነሳ፡ ኢሳትን ለማቋረጥ ማናቸውንም ሙከራ እንደሚያደርግ ገልጻ፡ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ኢሳት እንዳይቋረጥና ጠንክሮ እንዲቀጥል የቻሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ አሳስባለች። በየጊዜው በኢሜይልና በስልክ የሚደርሱንን አስተያየቶች እንዘግብላችኋለን።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ