Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 9 ቀን 2002 ዓ.ም. June 16, 2010) ባለፈው ሣምንት ማክሰኞ ከአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ወደ ቴልሰቪቭ ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ35 ላይ ይበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ለአርባ አምስት ደቂቃ ያህል እንዲዘገይ ተደረገ። ይህም የሆነው በደህንነት ሰዎች የተጠረጠሩ ሁለት ተሳፋሪዎችን ተጨማሪ ፍተሻ ሲደረግላቸው መሆኑ ታወቀ።

 

በዕለቱ በደህንነት ሰዎች የተጠረጠሩት ሁለት ሰዎች ልዩና ከፍተኛ ፍተሻ የተደረገባቸው ሲሆን፣ በያዙት የእጅ ቦርሳ ውስጥ 10 ትናንሽ የክብሪት ሳጥኖች መገኘታቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል። ተሳፋሪዎቹ ተቀጣጣይ ነገር አውሮፕላን ውስጥ ይዞ መግባት አይቻልም ተብለው ክብሪቶቹን ከተነጠቁ በኋላ ዘግይተው እንዲሳፈሩ ተደርጓል። በዚህም ምክንያት ከምሽቱ 4፡35 ሰዓት ላይ መነሳት የነበረበት አውሮፕላን 5፡10 ሰዓት ላይ እንዲበር ተደርጓል።

 

በምስራቅ አፍሪካ የሽብረተኞች እንቅስቃሴን በመስጋት የእስራኤል መንግሥት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሁለት ዓመት በፊት ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገውን በረራ ለማቆም ወስኖ የነበረ ቢሆንም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዩ ጥበቃ አደርጋለሁ በሚል ቃል ስለገባለት በረራውን እንዲቀጥል ማድረጉ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት በተለይ ወደ እስራኤል የሚበረው አውሮፕላን ሲነሳ በመኪና ሳይቀር ልዩ አጀብ እንደሚደረግለት ታውቋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ