ካናዳዎችና አውሮፓዎችም ከእጣው ተጋርተዋል

ከጁላይ 29 እስከ ጁላይ 31 በአምስተርዳም በተካሄደው 8ኛው የኢትዮጵያዊያን አውሮፓውያን ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ እንዲወጣ ታስቦ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (በምህጻረ ቃሉኢሳት”) መርጃ የተዘጋጀ ቶምቦላ ቅዳሜ ጁላይ 31 ቀን ከምሽቱ 8 ሰዓት አካባቢ አያሌ የኢሳት ደጋፊዎችና ጥቂት ተቃዋሚዎች በተገኙበት ወጣ።

 

በዚህ እጣ ከተዘጋጁት 4000 ትኬቶች ውስጥ፡ በመረጃ ስህተት ምክንያት ሳይሸጥ ከቀረው 6 ትኬት ውጪ ከሶስት ሺህ በላይ ትኬት መሸጣቸውን የገለጹት የቶምቦላው አዘጋጆች፡ በወጣው እጣ መሰረት የመጀመሪያ እጣ የሆነውን 42 ኢንች ዝርግ ቴሌቪዥን ቁጥር 1341 ከአሜሪካ ወስዶታል።

ሁለተኛው ላፕቶፕ ቁጥር 3662

ሶስተኛው እጣ አይፎን 3 ደግሞ ቁጥር 1951 ሆኗል።

በዚህ ካናዳምአውሮፓም ከአሜሪካኖቹ ጋር በተጋሩት እጣ፡ የወጡት ቁጥሮች እንደሚከተለው ናቸው።

4ኛው እጣ፡ ኮንሶል፡ 3454

 5ኛው ቪዲዮ ካሜራ እጣ፡ 2420 

6ኛው 20 ኢንች ዝርግ ሞኒተር እጣ፡ 2234

7ኛው ዲጂታል ካሜራ፡ 188  

8ኛው ጂፒኤስ፡ 2743

  9ኛው አይፖድ ናኖ፡ 627  

10ኛውና 11ኛው እጣዎች የኮምፒውተር ማዳመጫዎች ሲሆኑ ቁጥሮቹም 387 እና 3664 ናቸው።

 12 እስከ 15ኛው እጣዎች ብሉ ቱዞች ሲሆኑ፡ ቁጥሮቹም፡ በተከታታይ 1621 3458 2189 እና 165 ናቸው።

በኢሳት ገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴ በጸደቀውና በኢሳት ደጋፊዎች ራስ አነሳሽነት የተዘጋጀው ቶምቦላ ከፍተኛና አስደሳች የህዝብ ምላሽ እንደታየበት ገልጸው እነዚህን ቁጥሮች የያዙ ሰዎች ቁጥራቸውንና ትኬታቸው ይዘው እየቀረቡ ሽልማቶቹን መቀበል እንደሚችሉ ገልጸዋል።

በዚህ ዝግጅትና የኢሳት ድንኳን አካባቢ ሆኖ ሲታዘብ የቆየው የዚህ አጭር ዘገባ አቀናባሪ፡ አንዳንድ ሰዎች በኢሳት መመስረት ከመደሰታቸው የተነሳ አራት አምስት ትኬት እየገዙእጣው ከወጣ ለኢሳት ይሁንእያሉ ትኬታቸው ለአዘጋጆቹ ትተው ሱሄዱ ተመልክቷል። እናቶች ልጆቻቸው ከኢሳት በረከት እንዲቋደሱ እጣውን እንዲያወጡ አሰልፈዋቸው ነበር።

የእጣው አወጣጥ ስነ ስርአት በቪዲዮ ካሜራ የተቀረጸ ሲሆን፡ አዘጋጆቹ አርትኦቱን እንደጨረሱ ለእይታ እንደሚአቀርቡት ጠቁመዋል። 

 

አምስተርዳም ሀምሌ፡(ጁላይ 31) 2010           

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ