በትናንቱ ፍንዳታ ሦስት ሰዎች ሞቱ፣ 11 ሰዎች ቆሰሉ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሚያዝያ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. April 15, 2008)፦ ትናንት አመሻሹ ላይ ወደ አስራ ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ነዳጅ ማደያዎች ላይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ የሦስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አስራ አንድ ሰዎች መቁሰላቸውን ከአዲስ አበባ ዛሬ ጠዋት የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የደረሰው መረጃ ጠቆመ።
ንብረትነቱ የሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲንን (በዋናነት)፣ የአቶ አብነት ገ/መስቀልና የአቶ ታደሰ ጥላሁን የተባሉ አንድ ሌላ ግለሰብ የሆነው ናሽናል ኦይል ኩባንያ (ኖክ) በተባለው ነዳጅ ማደያ እንደሆነ ትናንት መዘገባችን አይዘነጋም። (የትናንቱን ሙሉ ዘገባ አስነብበኝ)



