Yod Abyissinia Traditional Restaurant on fireEthiopia Zare (ኀሙስ ሚያዝያ 9 ቀን 2000 ዓ.ም. April 17, 2008)፦ አዲስ አበባ ውስጥ በሚኪሌላንድ መንገድ የሚገኘውና የአቶ ትዕዛዙ ኮሬ ንብረት የሆነው "ዮድ አቢሲኒያ የባሕል ምግብ ቤት" ትናንት ሚያዝያ 8 ቀን 2000 ዓ.ም. በደረሰ የእሳት አደጋ ምግብ ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ወደመ።

 

 

Yod Abyissinia Traditional Restaurant on fire

 

 

ከኤሌክትሪክ ምሰሶ ላይ ተቆርጦ በሆቴሉ ጣሪያ ላይ በወደቀ ገመድ ምክንያት የተነሳው ይኸው የእሳት ቃጠሎ የ"ዮድ አቢሲኒያ የባሕል ምግብ ቤት"ን ሙሉ ለሙሉ አውድሞት ከፍተኛ የንብረት ጉዳት ማድረሱ ታውቋል።

ምግብ ቤቱ በባሕላዊ መንገድ ተሠርቶ የነበረ በመሆኑ ሸንበቆ፣ በድር፣ በእንጨት፣ ... የተሠራ በመሆኑና በርካታ ለጌጥነት ተሰቅለው የነበሩ ባህላዊ ቅርፃ ቅርፆች ስለነበሩ ለቃጠሎው መባባስ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ማድረጋቸው ታውቋል።

የአራዳ እሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእሳት አደጋ ተረባብረው እሳቱን ለማጥፋት አንድ ሰዓት ተኩል እንደወሰደባቸው ታውቋል።

 

የባሕል ምግብ ቤቱ ሥራ ከጀመረ አራት ዓመት የሆነውና ለ75 ሠራተኞች የሥራ ዕድል ሰጥቶ ይንቀሳቀስ እንደነበር ታውቋል። አቶ ትዕዛዙ ኮሬ በቅርቡ ብሥራተ ገብርኤል እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ተጨማሪ ምግብ ቤት ለመክፈት እየተዘጋጁ እንደሆነ ይነገራል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ