አውስትራሊያ ዜጎቿን አስጠንቅቃለች

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 18 ቀን 2003 ዓ.ም. January 26, 2011)፦ በቅርቡ የሚከፈተውን የአፍሪካ አንድነት ጉባኤ ተከትሎ የሽብር ጥቃት በአዲስ አበባ ሊደርስ እንደሚችል ታማኝ መረጃዎችን እንደሰበሰበች አውስትራሊያ አስታወቀች።

 

ተጋባዥ ተናጋሪ የሆኑት የፈረንሳይ ትሬዚዳንት ኒኮላ ሳርኮዚን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ርዕሳነ ብሄራት እንደሚገኙበት የተገለጸው የአፍሪካው ህብረት ጉባኤ በሚካሄድባት አዲስ አበባ ከተማ በተለይ የውጭ ዜጎች ይበዙባቸዋል በተባሉ ቦታዎች የሽብር ጥቃቶቹ ኢላማዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገልጿል።

 

ጉባኤው ላይ ለመሳተፍና አዲስ ኢምባሲ በኢትዮጵያ ለመክፈት የአውስትራሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ወደ አዲስ አበባ ባቀኑበት በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የጉብኝት፣ ስራና ንግድ ስራዎች ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ የሚያመሩ ዜጎቿን ያስጠነቀቀችው አውስትራሊያ ጥቃቱን ሊያደርሱ የሚችሉት አክራሪዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁማለች።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ