እነአቶ አንዳርጋቸው፣ መስፍን አማን፣ ዳንኤል አሰፋና ቸኮል ጌታሁንም አሉበት

Ethiopia Zare (ኀሙስ ሚያዝያ 16 ቀን 2000 ዓ.ም. April 24, 2008) ዶ/ር ብርሃኑና ሌሎች አራት የቅንጅት አመራር አባላት በቀድሞው ቅንጅትም ሆነ አሁን በአገዛዙ አፈና ስማቸው ተወስዶባቸው በሌላ ስም ለመንቀሳቀስ ከወሰኑትና ራሳቸውን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህና ብለው ከሰየሙ የቅንጅት አባላት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸውና ራሳቸውን ያገለሉ መሆኑን ዛሬ ባወጡት መግለጫ ገለጹ።



ዶ/ር ብርሃኑን ጨምሮ አራቱ ማለትም አቶ መስፍን አማን፣ አቶ ዳንኤል አሰፋ፣ አቶ ቸኮል ጌታሁን እና አቶ አንዳርጋቸው ከአሁን በኋላ በቅንጅት ስም እንደማይንቀሳቀሱና የራሳቸውን የትግል ስልት ይዘው እንደሚቀጥሉ የገለጹ ሲሆን፤ ወያኔን ሳይወድ በግዱ ወደ ድርድር እንዲመጣ ሊያስገድድ በሚችል መልኩ ራሳቸውን አጠናክረው ለመታገል እንደወሰኑም ለማወቅ ችለናል። መግለጫውን አስነብበኝ (PDF)

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ