በቶሮንቶ ስብሰባ ጁዋር መሀመድ፣ ኦባንግ ሜቶ፣ አቶ መሐመድ ሐሰንና አበበ በለው ይናገራሉ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 29 ቀን 2003 ዓ.ም May 5, 2011)፦ ብዙ ኢትዮጵያዊያኖች ይኖሩበታል በተባለለት ቶሮንቶ ከተማ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪው ወጣት ጁዋር መሐመድ፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪው ኦባንግ ሜቶ፣ አቶ መሀመድ ሀሰንና የአዲስ ድምጽ ራዲዮ አስተናጋጅ አበበ በለው የሚገኙበት ህዝባዊ ስብሰባ መሰናዳቱንና የአባይ ግድብን በሚመለከት ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ አዘጋጆቹ በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

 

ተናጋሪዎቹ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ሲሆን ወጣቱ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ ጁዋር መሀመድ የህብረትን አስፈላጊነትና ልዩነትን፣ አቻችሎ በአንድ ላይ መታገል ውጤቱ አጭር እንደሚያደርገው አመላካች በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚአደርግ ታውቋል።

 

የካናዳ ኦጋዴን አድቮከሲ መስራች የሆኑት አቶ መሐመድ ሐሰን፣ አቶ መለስ በሶማሌ ጦርነት ወቅት ከጠላት ወግነው ሀገራቸውን የወጉ ፋሽስት መሆናቸውን በማስረጃ የተደገፈ ጥናታቸውን እንደሚያቀርቡ የተገለጸ ሲሆን የአኙዋክ ህዝብን አሰቃቂ እልቂት ለአለሙ ማህበረሰብ በማጋለጥና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በመቃወም የሚታወቀው ኦባንግ ሜቶ ደግሞ በአሁኑ ሰአት በኢትዮጰያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የባእዳን መሬት ንጥቂያ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን የአዲስ ድምጹ አበበ በለው በመገናኛ ብዙሀን ላይ የሚደረገውን አፈናና የመገናኛ ብዙሀን አስፈላጊነት ዙሪያ እንደሚናገር ከመታወቁም በላይ በተለይ በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አነጋጋሪ በሆነው በአባይ ዙሪያ ሊደርግ የሚገባውን አቋም፣ ህዝብ በእኩልነት የሚኖርባትን ነጻ ኢትዮጵያ ለመገንባት የኢህአዴግ አገዛዝ በሚሰጠን የቤት ስራ መወጠር እንደሌለብን እንደሚያብራራ ታውቋል።

 

ይህ በቶሮንቶ ሚካሄደው ስብሰባ አርብ እንግዶቹን በመቀበል በሚደረግ መለስተኛ ውይይት የሚጀመር ሲሆን ዋናው ህዝባዊ ጉባኤ ቅዳሜ May 7/2011 ዓም 40 Donalds ላይ ከ2pm ጀምሮ እንደሚካሄድ ታውቋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ