ሁለት ሰራተኞች የደረሱበት አልታወቀም

Ethiopia Zare (ረቡዕ ግንቦት 10 ቀን 2003 ዓ.ም. May 18, 2011)፦ ባለፈው ሳምንት አርብ አንድ የአለም አቀፉ የምግብ ድርጅት ሰራተኛ ባልታወቁ ታጣቂዎች ከተገደለና ሁለት ተጨማሪ ሰራተኞች መጥፋታቸው ከተገለጸጸ ወዲህ ገዥው መንግስትና በተቃዋሚው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጸጻነት ግንባር የተካረረ ሰጣ ገባ ጀምረዋል።

 

ገዥው የኢህአዴግ መንግስት ለተገደለውም ሆነ ለጠፉት ሁለት የአለም አቀፉ የምግብ ድርጅት ሰራተኞች ተጠያቂው ኦብነግ የተባለው አሸባሪ ድርጅት ነው በማለት ተደጋጋሚ ክስ ያቀረበ ሲሆን በተጻራሪው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግምባር ድርጊቱን የፈጸመውና ጥቃቱን ያደረሰው የኢህአዴግ መንግስት ነው በማለት ምላሽ ሰጠጥቷል።

 

የሰባት ልጆች አባት የሆነውና ቤተሰብ አስተዳዳሪ የነበረው ፈረኻን ሀምሳ በምግቡ ድርጅት ከ2006 ጀምሮ ህይወቱን በጥቃቱ እስካጣበት ጊዜ ድረስ በሾፌርነት ያገለገለ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በአርብ እለቱ ጥቃት የደረሱበት ያልታወቁት ሁለት ሰራተኞችን በሚመለከትም ምንም አይነት መረጃ እንዳልተገኘ ታውቋል። ጥቃቱ የደረሰበት ቦታ ተደጋጋሚ ግጭት የሚከሰትበት የኢጋዴን አካባቢ ሲሆን ለጥቃቱ እስከ አሁን ሀላፊነቱን የወሰደ የለም።

 

የአለም አቀፍ የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጆሴቴ ሽራን በድርጊቱ እጅግ ልባቸው እንዳዘነ ገልጸው የምግብ እርዳታ ሰራተኞች ከለላ የሚያስፈልጋቸውና የብዙዎችን ህይወት ለመታደግ በየቦታው የሚንከራተቱ እንደመሆነናቸው የአለም ማህበረሰብ ለእንዲህ አይነቱ ጥቃት ፈጣን እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል።

 

የአለም አቀፉ ምግብ ድርጅት በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በርካታ የእርዳታ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝና በተለይ በኢትዮጵያ ብቻ ለ4.5 ሚሊዮን ህዝብ የምግብ እርዳታ ለማድረስ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ