የአንድነት ኃይሎች ስብሰባ በቶሮንቶ
(ዘጋቢ፡ መላኩ አወቀ)
በኢሕአፓ(ዴ) የቶሮንቶና አካባቢው የድጋፍ ኮሚቴ አባላት አዘጋጅነትና በአንድነት ኃይሎች፤ በሲቪክ ማኅበራትና ታዋቂ ግለሰቦች ትብብርና ግምባር-ቀደምነት ወደፊት ሊመሠረት የታሰበውን ሕብረት እውን ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ በቆዩትና አሁን እያደረጉ ባሉት አሰባሳቢ የሲቪክ ማኅበራት፤ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችና ግለሰቦች ትብብር ሜይ 14, 2011 (እ.ኤ.አ) በቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ብዙ ሰዓት የወሰደና አወያይና ተወያይ ልብ ከልብ የተገናኙበት ስብሰባ ተደርጓል።
ስብሰባውንም በእንግዳ ተናጋሪነትና በቁልፍ አወያይነት ህይወት ሰጥተው የመሩት ዶ/ር ወንድሙ መኮንን (ከሎንዶን፤ እንግሊዝ)፣ አቶ መሥፍን ተፈራ (ከኢሕአፓ(ዴ) አመራር ም/ቤት) እና ዶ/ር ቡሻ ታዓ (ከቶሮንቶ) ሲሆኑ፤ በሰብሳቢነት ደግሞ አቶ ለይኩን ተሾመ (የኢሕአፓ(ዴ) አመራር ም/ቤት አባል) ነበሩ። የዕለቱ ስብሰባም የተጀመረው ለኢትዮጵያ ሠላምን፣ ዴሞክራሲንና ፍትህን ለማስገኘት በግምባር ቆመው ሲታገሉ ለወደቁ ብዙ ሺ ሰማዕታት የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጎ ነበር። ... (ሙሉውን ዘገባ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



